መደብ:Tesfaye Gabisso

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ በአንተ ድኛለሁ ነፃ ወጥቻለሁ ተመስገን ኢየሱስ እልሃለሁ

                         ቀርቦ የሚያፅናና በጠፋበት
                         መከራው በዝቶ ባየለበት
                         ጌታዬ ነበርክ ከዚያ ስፍራ
                         እያፅናናኸኝ እንዳልፈራ

ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ በአንተ ድኛለሁ ነፃ ወጥቻለሁ ተመስገን ኢየሱስ እልሃለሁ

                         በሌለህበት የሚያረካ ነገር
                         ከዚያ በርሀ በደረቅ ምድር
                         የህይወት ተስፋ ሆነኸኛል
                         ከአለት ውሃ አፈለክልኝ

ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ በአንተ ድኛለሁ ነፃ ወጥቻለሁ ተመስገን ኢየሱስ እልሃለሁ

                         አውሎ ንፋስ እየነፈሰ
                         ማዕበሉ እያተራመሰ
                         ወደ እኔ የደረሰ ሲመስለኝ
                         በህይወቴ ስሰጋ ሳለሁኝ

ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ በአንተ ድኛለሁ ነፃ ወጥቻለሁ ተመስገን ኢየሱስ እልሃለሁ

                         ግራ ቀኜን ባይ ዙሪያው አጥር
                         ሆኖብኝ ነበር ኑሮ በምድር
                         መውጫ ከሌለው ዝግ ቦታ
                         አንተ አወጣኸኝ የኔ ጌታ

ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ በአንተ ድኛለሁ ነፃ ወጥቻለሁኝ ተመስገን ኢየሱስ እልሃለሁ

                         ለአስጨናቂዎች ሳልገዛ
                         ስለበዛልኝ ያንተ እገዛ
                         ወጥቻለሁ ቅጥሩ ፈርሶ
                         የወሰንከውም ጊዜ ደርሶ

ግሩም አባት ነህ የምትራራ የምትረዳኝ በመከራ በአንተ ድኛለሁ ነፃ ወጥቻለሁ ተመስገን ኢየሱስ እልሃለሁ x2

በምድብ «Tesfaye Gabisso» ውስጥ የሚገኙ ገጾች

በዚሁ መደብ ውስጥ (ከ114 በጠቅላላ) የሚከተሉት 114 መጣጥፎች አሉ።