From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በህዝቡ ፡ ሁሉ ፡ የሚሆን
የምሥራች ፡ ተነገረ
ታላቅ ፡ ደስታ ፡ ነው ፡ ልደቱ
ይዘምር ፡ እስኪ ፡ ፍጥረቱ
አዝ፦ መጣ ፡ በራልን ፡ (በራልን)
ጌታ ፡ ሊጐበኘን ፡ (ሊጐበኘን)
ቤዛ ፡ ሊሆንልን
ከኃጢያት ፡ እኛኑ ፡ ሊያድን
ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነና ፡ ከድንግል ፡ ተወለደልን
ህጻን ፡ ተወለደ ፡ ለእኛ
በቤተልሔም ፡ በረት ፡ ተኛ
ለኃጥያተኞች ፡ መዳኛ
ሊሆን ፡ የበጐች ፡ እረኛ
አዝ፦ መጣ ፡ በራልን ፡ (በራልን)
ጌታ ፡ ሊጐበኘን ፡ (ሊጐበኘን)
ቤዛ ፡ ሊሆንልን
ከኃጢያት ፡ እኛኑ ፡ ሊያድን
ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነና ፡ ከድንግል ፡ ተወለደልን
ሥሙ ፡ የተመሰገነ
ክርስቶስ ፡ ጌታ ፡ የሆነ
ተገልጧልና ፡ ልዑሉ
ስገዱለት ፡ ዕልል ፡ በሉ
አዝ፦ መጣ ፡ በራልን ፡ (በራልን)
ጌታ ፡ ሊጐበኘን ፡ (ሊጐበኘን)
ቤዛ ፡ ሊሆንልን
ከኃጢያት ፡ እኛኑ ፡ ሊያድን
ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነና ፡ ከድንግል ፡ ተወለደልን
ተሽቀዳደሙ ፡ ኑ ፡ እዩት
የሚመስልህ ፡ የለም ፡ በሉት
አድንቁት ፡ እጅግ ፡ አክብሩት
ይገባዋል ፡ አመስግኑት
አዝ፦ መጣ ፡ በራልን ፡ (በራልን)
ጌታ ፡ ሊጐበኘን ፡ (ሊጐበኘን)
ቤዛ ፡ ሊሆንልን
ከኃጢያት ፡ እኛኑ ፡ ሊያድን
ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነና ፡ ከድንግል ፡ ተወለደልን
በላይ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ክብር
ለእኛም ፡ ሰላም ፡ በምድር
ይሁን ፡ ብለን ፡ እንዘምር
እረፍት ፡ አለ ፡ መስቀሉ ፡ ስር
አዝ፦ መጣ ፡ በራልን ፡ (በራልን)
ጌታ ፡ ሊጐበኘን ፡ (ሊጐበኘን)
ቤዛ ፡ ሊሆንልን
ከኃጢያት ፡ እኛኑ ፡ ሊያድን
ቃል ፡ ሥጋ ፡ ሆነና ፡ ከድንግል ፡ ተወለደልን
|