From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አቤቱ ፡ ጌታችን፣ እስኪ ፡ እናመስግንህ
ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ "ክበር" ፡ እንበልህ
ሰይጣን ፡ እንደ ፡ ስንዴ ፡ ሊያበጥረን ፡ ሽቶ
ዕምነት ፡ ተስፋችንን ፡ ሊያጨልም ፡ ዝቶ
አምርሮ ፡ ቢነሣም ፡ እጅግ ፡ ተቆጥቶ
ተገዝቶ ፡ አየነው ፡ በአንተ ፡ ድል ፡ ተነሥቶ
ስለ ፡ ዕምነታችን ፣ ስለ ፡ ሕይወታችን
የተሟገትክልን ፣ ተመስገን ፡ ጌታችን
የተጓዝንበትን ፡ መንገድ ፡ ሊያቋርጥ
ጠላታችን ፡ አልፎ፡ እንቅፋት ፡ ቢያስቀምጥ
የተመሸገውን ፡ ከፍ ፡ ያለውን ፡ ቅጥሩን
አፈራርሰህ ፡ ጣልከው ፡ ኢየሱስ ፡ ተመስገን
አንተ ፡ ቅን ፡ የሆነን፡ መንገድ ፡ ታቀናለህ
የተዘጋውንም ፡ በር ፡ ትከፍትልናለህ
የሕዝብህን ፡ ስድብ ፡ ከምድር ፡ አስወግደህ
ከፊታቸውም ፡ ላይ ፡ እንባቸውን ፡ አብሰህ
ራሣቸውን ፡ በዘይት ፡ በሞገስ ፡ ቀብተህ
በምሥጋናቸውም ፡ አንተ ፡ ትነግሣለህ
ለታናሹ ፡ መንጋ ፡ በዝቷል ፡ ቸርነትህ
ክበር ፡ አምላካችን ፡ ዘላለም ፡ ልዑል ፡ ነህ
ግብዣን ፡ አዘጋጅተህ ፡ በክብር ፡ ጠራኸን
በንጉሥ ፡ ገበታ ፡ ይኸው ፡ አስቀመጥከን
በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ በከበረው ፡ ሥፍራ
ነፍሣችን ፡ ጠገበች ፡ ከሕይወት ፡ እንጀራ
ፈቅደን ፡ ከልባችን ፡ እናመልክሃለን
ለዘለዓለሙም ፡ ለአንተ ፡ እንገዛለን
|