From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በበረታው ፡ ክንድ ፡ በበረታችም ፡ እጅ
በጌታ ፡ መዳኑን ፡ ከሞት ፡ ከሲዖል
እንደምን ፡ ዘንግቶ ፡ ሰው ፡ ያጉረመርማል
ወንድሙን ፡ ለመውደድ ፡ እጁን ፡ ይዘረጋል
አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ
ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈሶ
ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ
ጥርሱን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x)
ስፍራውን ፡ ለቆ ፡ ሲሄድ ፡ ለመጉደፍ ፡ ሲቸኩል
ትህትናውን ፡ አውልቆ ፡ ለሞት ፡ ሲንቀለቀል
እዪት ፡ ያንን ፡ ዝንጉ ፡ ቃል ፡ ኪዳኑን ፡ ሲያፈርስ
በአመጻው ፡ ምክንያት ፡ ፍቅርን ፡ ሲያቀዘቅዝ
አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ
ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈሶ
ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ
ጥርሱን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x)
አንተን ፡ እየፈራሁ ፡ ቀኑን ፡ ሁሉ ፡ ልኑር
ትህትናም ፡ አይራቀኝ ፡ አልነፈግህ ፡ ፍቅር
እጅህ ፡ እንዳይመታኝ ፡ አጉል ፡ ደፋር ፡ ሆኜ
መተረቻ ፡ እንዳልሆን ፡ በሃፍረት ፡ ተሸፍኜ
አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ
ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈሶ
ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ
ጥርሱን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ
አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x)
|