ቤዛ ፡ የሆንክልኝ (Bieza Yehonkelegn) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(7)

ያይሃል
(Yayehal)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ ቤዛ ፡ የሆንክልኝ ፡ ጌታዬ
የሕይወቴ ፡ መልሕቅ ፡ ድጋፍ ፡ የዕርምጃዬ
ማዳንህ ፡ ተገልጾ ፡ አይቻለሁ ፡ ጽድቅህን
ስለዚህ ፡ በደስታ ፡ ላመስግን ፡ ስምህን (፪x)

በወርቅ ፡ ይሁን ፡ በብር ፣ በጥበብ ፣ በዕውቀት
የዳነ ፡ ማን ፡ አለ ፡ ከኃጢአት ፡ ውድቀት?
ጌታ ፡ ሆይ ! አንተ ፡ ነህ ፡ ጽድቅን ፡ ያለበስኸኝ
በምሕረት ፡ አማልደህ ፡ ከዓብ ፡ ያስታረቅኸኝ (፪x)

አዝ፦ ቤዛ ፡ የሆንክልኝ ፡ ጌታዬ
የሕይወቴ ፡ መልሕቅ ፡ ድጋፍ ፡ የዕርምጃዬ
ማዳንህ ፡ ተገልጾ ፡ አይቻለሁ ፡ ጽድቅህን
ስለዚህ ፡ በደስታ ፡ ላመስግን ፡ ስምህን (፪x)

በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ የመስቀል ፡ ላይ ፡ ሥራ
ከዘለዓለም ፡ ሞት ፡ ዳንኩኝ ፡ ከመከራ
በነጻ ፡ ታድዬ ፡ የጽድቅን ፡ ሥጦታ
ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ ፡ ለተቤዠኝ ፡ ጌታ (፪X)

አዝ፦ ቤዛ ፡ የሆንክልኝ ፡ ጌታዬ
የሕይወቴ ፡ መልሕቅ ፡ ድጋፍ ፡ የዕርምጃዬ
ማዳንህ ፡ ተገልጾ ፡ አይቻለሁ ፡ ጽድቅህን
ስለዚህ ፡ በደስታ ፡ ላመስግን ፡ ስምህን (፪x)

ብላቴንነቴን ፣ ድካሜን ፡ ገምተህ
አንተ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ተገልጠህ
የበረታብኝን ፡ ጠላቴን ፡ ቀጥቅጠህ
ድል ፡ ያጐናተጸፍኸኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)

አዝ፦ ቤዛ ፡ የሆንክልኝ ፡ ጌታዬ
የሕይወቴ ፡ መልሕቅ ፡ ድጋፍ ፡ የዕርምጃዬ
ማዳንህ ፡ ተገልጾ ፡ አይቻለሁ ፡ ጽድቅህን
ስለዚህ ፡ በደስታ ፡ ላመስግን ፡ ስምህን (፪x)

መልካሙን ፡ ሥራህን ፡ በሕይወቴ ፡ ፈጽመህ
እንድትታይብኝ ፡ በኑሮዬ ፡ ጐልተህ
ይህ ፡ ነው ፡ ልመናዬ ፡ የዘወትር ፡ ጸሎቴ
ክብሬ ፣ ዕርካታዬ ፣ አንተ ፡ ነህ ፡ ትምክህቴ (፪x)

አዝ፦ ቤዛ ፡ የሆንክልኝ ፡ ጌታዬ
የሕይወቴ ፡ መልሕቅ ፡ ድጋፍ ፡ የዕርምጃዬ
ማዳንህ ፡ ተገልጾ ፡ አይቻለሁ ፡ ጽድቅህን
ስለዚህ ፡ በደስታ ፡ ላመስግን ፡ ስምህን (፪x)