ጓዳችንን ፡ አጽዳ (Guadachenen Atseda) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
Broom.png ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፸ ፬ ((2012))
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 4:47
ጸሐፊ (Writer):
(tesfaye gabiso
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

እራስህን ፡ ንቀን ፡ ቃልህን ፡ አቃለን
መንፈስህ ፡ ሲወሰን ፡ ሁሌ ፡ እንሰማለን
ሥጋ ፡ ብቻ ፡ ሆነን ፡ በአመፅ ፡ ተውጠናል
እራስን ፡ መመርመር ፡ ፍፅም ፡ አቅቶናል

አዝ፦ በከፍታ ፡ ስፍራ ፡ በሰማይ ፡ ያለኸው
ምንም ፡ አይሳንህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንከው
ልብ ፡ ኩላሊትን ፡ የምትመረምረው
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጓዳችንን ፡ አፅዳ ፡ አጥበህ ፡ አስተካክለው

ያኔ ፡ ስትልከን ፡ ጦር ፡ እቃህን ፡ ሰጥተህ
ኃይል ፡ በኃይል ፡ አድርገህ ፡ ሞገስ ፡ አከናንበህ
ከጦር ፡ ሜዳው ፡ ወጥተን ፡ ድልን ፡ ሰጥተኸናል
ዛሬ ፡ ግን ፡ ወዮልን ፡ ጠላት ፡ ዝቶብናል

አዝ፦ በከፍታ ፡ ስፍራ ፡ በሰማይ ፡ ያለኸው
ምንም ፡ አይሳንህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንከው
ልብ ፡ ኩላሊትን ፡ የምትመረምረው
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጓዳችንን ፡ አፅዳ ፡ አጥበህ ፡ አስተካክለው

እንደ ፡ ቀድሞ ፡ መስሎን ፡ እንዋጋ ፡ ብንል
በብዙ ፡ ለማጥመድ ፡ መረቡን ፡ ብንጥል
ከንቱ ፡ ልፋት ፡ እንጂ ፡ ምርኮ ፡ ከየት ፡ ይምጣ
ግራ ፡ ተጋብተናል ፡ በከንቱ ፡ እሩጫ

አዝ፦ በከፍታ ፡ ስፍራ ፡ በሰማይ ፡ ያለኸው
ምንም ፡ አይሳንህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንከው
ልብ ፡ ኩላሊትን ፡ የምትመረምረው
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጓዳችንን ፡ አፅዳ ፡ አጥበህ ፡ አስተካክለው

አሁን ፡ ተረድተናል ፡ ኃጢአት ፡ አድርገናል
በትዕቢት ፡ ፍላጻ ፡ አስለቅሰናል
በእርማችን ፡ ምክንያት ፡ ፊትህ ፡ ከብዶብናል
ጌት ፡ ሆይ ፡ ታረቀን ፡ ማረን ፡ ብለንሃል

አዝ፦ በከፍታ ፡ ስፍራ ፡ በሰማይ ፡ ያለኸው
ምንም ፡ አይሳንህ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንከው
ልብ ፡ ኩላሊትን ፡ የምትመረምረው
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጓዳችንን ፡ አፅዳ ፡ አጥበህ ፡ አስተካክለው