ዝም ፡ ብዬ ፡ እቆማለሁ (Zem Beyie Eqomalehu) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(1)

አልበም
(1988)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 3:47
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

በዚች ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ አለብኝ
አኔ ፡ ዝም ፡ አላለሁ ፡ አንተ ፡ ተዋጋልኝ
አንተን ፡ ያሰለፉ ፡ ስልፉ ፡ ሰምሮላቸው
አይቼ ፡ ተምሬያለሁ ፡ ከድል ፡ ዝማሬያቸው

አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ ፡ አቆማለሁ
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ለቃለሁ
በእምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አያለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ድልህን ፡ አጠብቃለሁ (፪x)

ሰልፉ ፡ የእኔ ፡ መስሎኝ ፡ አረታለሁ ፡ ብዬ
በሥጋዬ ፡ ስታገል ፡ ተዝለፍልፌ ፡ ዝዬ
መረታቴ ፡ ነው ፡ እኮ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
ኧረ ፡ ቶሎ ፡ ናልኝ ፡ አይብዛ ፡ መከራዬ

አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ ፡ አቆማለሁ
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ለቃለሁ
በእምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አያለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ድልህን ፡ አጠብቃለሁ (፪x)

የእሳት ፡ ሰረገላው ፡ መለኮታዊው ፡ ጦር
የድምፅህ ፡ ነጐድጓድ ፡ ጠላት ፡ የሚያሸብር
ይምጣ ፡ ይዋጋልኝ ፡ እኔ ፡ ኃይል ፡ የለኝም
አሁን ፡ አውቄያለሁ ፡ ሰልፉ ፡ የእኔ ፡ አይደለም

አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ ፡ አቆማለሁ
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ለቃለሁ
በእምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አያለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ድልህን ፡ አጠብቃለሁ (፪x)