ግሩም አባት ነህ (Girum Abat Neh) - Tesfaye Gabiso

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
Tesfaye Gabiso
(Tesfaye Gabisso)


ሌሎች ፡ ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Other Singles)
ሌሎች ፡ የTesfaye Gabiso ፡ አልበሞች
(Other Albums ፡ by Tesfaye Gabisso)

አዝ:- ግሩም አባት ነህ የምትራራ
የምትረዳኝ በመከራ
በአንተ ድኛለሁ ነፃ ወጥቻለው
ተመስገን ኢየሱስ እልሃለው

ቀርቦ ሚያጽናና በጠፋበት
መከራው በዝቶ ባየለበት
ጌታዬ ነበርክ በዚያ ስፍራ
እያጽናናሃኝ እንዳልፈራ

አዝ:-

በሌለበት የሚያረካ ነገር
ከዚያ በረሃ ደረቅ ምድር
የህይወት ተስፋ ሆነህልኝ
ከአለት ውሃ አፈለቅህልኝ

አዝ:-

አውሎ ንፋሥ እየነፈሰ
ማዕበሉ እያተራመሰ
ወደኔ የደረሰ ሲመስለኝ
በህይወቴ ስሰጋ ሳለሁኝ

አዝ:-

ግራ ቀኜን ባይ ዙሪያው አጥር
ሆኖብኝ ነበር ኑሮ በምድር
መውጫ ከሌለው ከዝግ ቦታ
አንተ አወጣሀኝ የኔ ጌታ

አዝ:-

ለአስጨናቂዎች ሳልገዛ
ስለበዛልኝ ያንተ እገዛ
ወጥቻለሁኝ ቅጥሩ ፈርሶ
የወሰንከውም ጊዜ ደርሶ