የአምላኩ ፡ ፈቃድ (Yeamlaku Feqad) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(6)

አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
(Abietu Mebareken Barken)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:25
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ
በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ
በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ
ጻድቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x)

የሥጋ ፡ ምኞት ፡ የዓይንም ፡ አምሮት
የዓለም ፡ ፍቅር ፡ ልቡን ፡ አታልሎት
በጌታ ፡ መሆን ፡ ሞኝነት ፡ መስሎት
ክርስትናዉን ፡ አውልቆ ፡ ጥሎት
ያንን ፡ ሰው ፡ እዩት ፡ ሲሮጥ ፡ ወደሞት

አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ
በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ
በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ
ጻድቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x)

የጌታን ፡ ፈቃድ ፡ ቀድሞ ፡ እየሮጠ
በምኞት ፡ ባሕር ፡ ገብቶ ፡ ተዋጠ
ዝናን ፡ ፍለጋ ፡ ሄደ ፡ ዋተተ
እርካታን ፡ ጥሎ ፡ እየከነፈ
እንደተጠማ ፡ ሳይረካ ፡ ሞተ

አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ
በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ
በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ
ጻዲቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x)

እንግዳው ፡ ሰው ፡ ሆይ ! የምድረበዳው
የማይረባህን ፡ የምትመኘው
ማንነትህን ፡ የዘነጋኸው
ምኞት ፡ ኃጢአትን ፣ ኃጢአት ፡ ሞትን
እንደምትወልድ ፡ እንዴት ፡ አጣኸው?

አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ
በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ
በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ
ጻድቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x)

የሥጋ ፡ ሩጫ ፡ ከእንግዲህ ፡ በቅቶ
ከንቱ ፡ መባከን ፡ ከእንግዲህ ፡ ቀርቶ
አርፈህ ፡ ተገዛ ፡ ፈቃዱን ፡ አውቀህ
የጌታን ፡ ምክር ፡ ቃሎቹን ፡ ንቀህ
እንዳትቀጣ ፡ ዳግም ፡ አምጸህ

አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ
በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ
በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ
ጻድቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x)