From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም
ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም
ታላቅነትህም ፡ ይነገር
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር (፪x)
ሕዝብህን ፡ ከምድር ፡ ዋጅተሃል
ታላቅ ፡ ሥራ ፡ ጀምረሃል
ሀሳብህ ፡ አይከለከልም
ፅድቅህ ፡ እውነትህ ፡ ይለምልም
አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም
ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም
ታላቅነትህም ፡ ይነገር
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር
በየደረስንበት ፡ ስፍራ
ስራችንን ፡ አንተ ፡ ሥራ
እጃችን ፡ ሳይዝል ፡ ስይደክም
ዛሬም ፡ እንደ ፡ ወትሮ ፡ ቅደም
አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም
ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም
ታላቅነትህም ፡ ይነገር
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር
ስለተነቀፈው ፡ ሥምህ
በምርኮ ፡ ስላለው ፡ ሕዝብህ
ይዘርጋ ፡ ያ ፡ ፅኑ ፡ ክንድህ
ዛሬም ፡ ይንሰራፋ ፡ ክብርህ
አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም
ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም
ታላቅነትህም ፡ ይነገር
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር
ወድቀን ፡ በፊትህ ፡ ስንጮህ
ክንድህ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ሰማይ ፡ ምድሩ ፡ ያከብርሃል
ሁሉም ፡ በፊትህ ፡ ይሰግዳል
አዝ፦ የሚቋቋምህ ፡ ማንም ፡ የለም
ፈቃድህ ፡ በእኛ ፡ ይሙላ ፡ ይፈፀም
ታላቅነትህም ፡ ይነገር
ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ክበር (፪x)
|