From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
ትላንትናም ፡ ዛሬ
እስከ ፡ ለዘለዓለም
ያው ፡ ነህ (፫x)
ሰማያት ፡ አርጅተው ፡ ከምድር ፡ ጋር ፡ ሲያልፉ
በውስጣቸው ፡ ያሉት ፡ ኃይላትም ፡ ሲጠፉ
አንተ ፡ ግን ፡ አቤቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያው ፡ ነህ
መለወጥ ፡ ሳያሻህ ፡ ደምቀህ ፡ ትኖራለህ
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
ትላንትናም ፡ ዛሬ
እስከ ፡ ለዘለዓለም
ያው ፡ ነህ (፫x)
እኛ ፡ የምናመልከው ፡ ሳይታክት ፡ ሳይደክም
በሥልጣኑ ፡ ገኖ ፡ ይኖራል ፡ ዘለዓለም
አልፋ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ዖሜጋም ፡ ነው ፡ ጌታ
በበረቱብን ፡ ላይ ፡ ክንዱ ፡ የበረታ
ሃሌ ፡ ሉያ! ሃሌ ፡ ሉያ! ሃሌ ፡ ሉያ!
ተጠብቀናል ፡ ታማኝ ፡ በሆነው
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ጉያ
ገና ፡ ኃጢአተኞች ፡ በደለኞች ፡ ሳለን
የእግዚአብሔርን ፡ ፍቅር ፡ በክርስቶስ ፡ አየን
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቱ ፡ የእኛን ፡ መርገም ፡ ወስዶ
ጽድቁን ፡ አልብሶናል ፡ ማቃችንን ፡ ቀዶ
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ
ትላንትናም ፡ ዛሬ
እስከ ፡ ለዘለዓለም
ያው ፡ ነህ (፫x)
በእኛ ፡ ላይ ፡ ያለው ፡ ከጥንትም ፡ ያሰብከው
ዛሬም ፡ እንዳየነው ፡ ዓላማህ ፡ ፍቅር ፡ ነው
በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ ኖረናል ፡ ተማምነን
በድል ፡ እንዘልቃለን ፡ በእጆችህ ፡ ተይዘን
ሃሌ ፡ ሉያ ! ሃሌ ፡ ሉያ ! ሃሌ ፡ ሉያ !
ተጠብቀናል ፡ ታማኝ ፡ በሆነው
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ጉያ
|