መብዛት ፡ መዋረዱን (Mebzat Mewaredun) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Tesfaye Gabisso Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ምህረቱ ፡ አያልቅምና
(Meheretu Ayalqemena)

ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 3:33
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ መብዛት ፡ መዋረዱን ፡ መራቡን ፡ መጥገቡን
ሁሉን ፡ ተምሬያለሁ ፡ ተመልክቸዋለሁ
ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ በክርስቶስ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ (፪x)

በቃሌ ፡ ስበትን ፡ በከንፈሬ ፡ ተሳስቼ ፡ እንዳልጥል
ያገኘሁት ፡ መስሎኝ ፡ እየከነፍኩ ፡ ስሮጥ ፡ ወደ ፡ ክፋት
ሰው ፡ ሁሉ ፡ አስፈርቶኝ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ አግኝቶኝ ፡ ያ ፡ ጌታ
እብድነቴን ፡ ገፎት ፡ ቤት ፡ ሰጠኝ ፡ አገኘሁ ፡ ይቅርታ

አዝ፦ መብዛት ፡ መዋረዱን ፡ መራቡን ፡ መጥገቡን
ሁሉን ፡ ተምሬያለሁ ፡ ተመልክቸዋለሁ
ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ በክርስቶስ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ (፪x)

እንደ ፡ ሰባ ፡ እንቦሳ ፡ ስፈነጥዝ ፡ በተራራ ፡ ሕይወት
ተመስገን ፡ እያልኩኝ ፡ ኢየሱስን ፡ በበረከት ፡ ምንጮች
ከዛም ፡ ሳላስበው ፡ በመቅሰፍት ፡ በሸለቆ ፡ ስገኝ
ተሰብሬ ፡ ሳለቅስ ፡ በጨለማ ፡ ብርሃን ፡ ሆንክልኝ

አዝ፦ መብዛት ፡ መዋረዱን ፡ መራቡን ፡ መጥገቡን
ሁሉን ፡ ተምሬያለሁ ፡ ተመልክቸዋለሁ
ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ በክርስቶስ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ (፪x)

ሰማያዊ ፡ ፀዳል ፡ ተገርስሶ ፡ የተነሳ ፡ ቢመስል
ከደብረዘይት ፡ መውረድ ፡ ልብን ፡ ቢያብሰለስል
ጌታ ፡ አልተለየኝም ፡ አብሮኝ ፡ አለ ፡ በሸለቆ ፡ ሕይወት
የተራሮች ፡ አምላክ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ አልሰጠኝም ፡ ለሞት

አዝ፦ መብዛት ፡ መዋረዱን ፡ መራቡን ፡ መጥገቡን
ሁሉን ፡ ተምሬያለሁ ፡ ተመልክቸዋለሁ
ኃይልን ፡ በሚሰጠኝ ፡ በክርስቶስ ፡ ሁሉን ፡ እችላለሁ (፪x)