From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የክሱን ፡ ክምችት ፡ የዕዳውን ፡ ጽህፈት
ደምስሰህልናል ፡ በመስቀልህ ፡ ምህረት
አንተ ፡ አጽድቀኸናል ፡ ማነው ፡ የሚከሰን
ከጸናችው ፡ እጅህ ፡ የለም ፡ የሚነጥቀን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተመሥገን
አዝ፦ አንተ ፡ የእውነት ፡ አምላክ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ከከሳሽ ፡ ያዳንከን ፡ ፈርደህልን ፡ ለእኛ
ጌታ ፡ ከመንበርህ ፡ ከጽድቅ ፡ ዙፋንህ
መድኃኒትን ፡ ልከህ ፡ በአንተ ፡ አርፏል ፡ ሕዝብህ
ተረታሁኝ ፡ ብሎ ፡ ጠላትም ፡ ባይተኛ
የማንተቀላፋ ፡ ጌታ ፡ አለህ ፡ ለእኛ
ደምፅህን ፡ ሲሰማ ፡ አጥማጅህ ፡ ገለል ፡ ይላል
ከመከራም ፡ ስጋት ፡ በአንተ ፡ ያመነ ፡ ያርፋል
ተከልሎ ፡ ይኖራል
አዝ፦ አንተ ፡ የእውነት ፡ አምላክ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ከከሳሽ ፡ ያዳንከን ፡ ፈርደህልን ፡ ለእኛ
ጌታ ፡ ከመንበርህ ፡ ከጽድቅ ፡ ዙፋንህ
መድኃኒትን ፡ ልከህ ፡ በአንተ ፡ አርፏል ፡ ሕዝብህ
ከሳሻችን ፡ ወድቆ ፡ እኛ ፡ ተነስተናል
ጉልበታችን ፡ ፀንቶ ፡ እነሆ ፡ ቆመናል
ታዳጊያችን ፡ ሆይ ፡ ተመሥገን ፡ እንበልህ
ከአዳኙ ፡ ወጥመድ ፡ የወጣን ፡ ሕዝበህ
ማርኮናል ፡ ፍቅርህ
አዝ፦ አንተ ፡ የእውነት ፡ አምላክ ፡ እውነተኛ ፡ ዳኛ
ከከሳሽ ፡ ያዳንከን ፡ ፈርደህልን ፡ ለእኛ
ጌታ ፡ ከመንበርህ ፡ ከጽድቅ ፡ ዙፋንህ
መድኃኒትን ፡ ልከህ ፡ በአንተ ፡ አርፏል ፡ ሕዝብህ
|