እምቢ (Embi) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(1)

እግዚአብሔር ፡ ኃያል
(Egziabhier Hayal)

ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 4:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

የሙታን ፡ ባልንጀራ ፡ ኃጢአተኛ ፡ ሳለሁ
ጌታን ፡ በማመኔ ፡ ከክፋት ፡ ድኛለሁ
ግን ፡ ሕይወቴን ፡ እንድክድ ፡ አሁን ፡ ብከተልም
ኢየሱሴን ፡ ክጄ ፡ ግኡዝ ፡ አላመልክም

አዝ፦ እምቢ ፡ አሻፈረኝ ፡ ለምስሉ ፡ አልሰግድም
ለሰው ፡ እጅ ፡ ሥራ ፡ አልንበረከክም
ከናቡከደናጾር ፡ የቁጣ ፡ ነበልባል
የማመልከው ፡ ጌታዬ ፡ በእርግጥ ፡ ያድነኛል

እቶኑ ፡ ይታየኛል ፡ ግለቱ ፡ ይሰማኛል
ፈርቼ ፡ አልጠላውም ፡ አንስቶ ፡ ያጠራኛል
ለሰማያዊው ፡ መንግሥት ፡ ብቁ ፡ ያደርገኛል
ሰው ፡ እንደሚያስበው ፡ መቼ ፡ ይጐዳኛል

አዝ፦ እምቢ ፡ አሻፈረኝ ፡ ለምስሉ ፡ አልሰግድም
ለሰው ፡ እጅ ፡ ሥራ ፡ አልንበረከክም
ከናቡከደናጾር ፡ የቁጣ ፡ ነበልባል
የማመልከው ፡ ጌታዬ ፡ በእርግጥ ፡ ያድነኛል

በእሳት ፡ ውስጥ ፡ ያሉትን ፡ ጭሱ ፡ ሳይነካቸው
አስረው ፡ የጣሏቸው ፡ ወላፈን ፡ ፈጃቸው
እንደዚህ ፡ የሚሰራ ፡ ኃያል ፡ ጌታ ፡ ካለኝ
ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ያንድድ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ቸገረኝ

አዝ፦ እምቢ ፡ አሻፈረኝ ፡ ለምስሉ ፡ አልሰግድም
ለሰው ፡ እጅ ፡ ሥራ ፡ አልንበረከክም
ከናቡከደናጾር ፡ የቁጣ ፡ ነበልባል
የማመልከው ፡ ጌታዬ ፡ በእርግጥ ፡ ያድነኛል

እምቢ (፫x)