ከሸካራው ፡ መንገድ (Keshekaraw Menged) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Tesfaye Gabisso Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ምህረቱ ፡ አያልቅምና
(Meheretu Ayalqemena)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 2:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ገና ፡ ህጻን ፡ ሳለህ ፡ ስጠነቀቅልህ
ክንዶችህን ፡ ይዤ ፡ ዳዴ ፡ ሳስተምርህ
መራመድን ፡ ችለህ ፡ ሩጫውን ፡ አጠናቅቀህ
እንዳልገሰገስክ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ታከተህ

አዝ፦ ከሸካራው ፡ መንገድ ፡ እግርህን ፡ መልሰው
አይበጅህምና ፡ ደሜን ፡ አትርገጠው
ይልቅ ፡ እንታረቅ ፡ ምህረቴ ፡ ብዙ ፡ ነው

በሃሩርር ፡ ተቃጥለህ ፡ በጥም ፡ ተመትተሃል
ፍሬህ ፡ ሁሉ ፡ ደርቆ ፡ ፍሬ ፡ ቢስ ፡ ሆነሃል
መንፈሳዊነትህ ፡ አሁን ፡ ከአንተ ፡ ርቆ
ለስጋ ፡ ተገዛህ ፡ ፀጋህ ፡ ሁሉ ፡ አልቆ

አዝ፦ ከሸካራው ፡ መንገድ ፡ እግርህን ፡ መልሰው
አይበጅህምና ፡ ደሜን ፡ አትርገጠው
ይልቅ ፡ እንታረቅ ፡ ምህረቴ ፡ ብዙ ፡ ነው
 
ከግብጽም ፡ ጀምሬ ፡ እኔ ፡ አምላክህ ፡ ነህ
በደሜ ፡ የዋጀሁህ ፡ ተው ፡ አታሳዝነኝ
ምህረት ፡ እንደምወድ ፡ ጸባዬን ፡ ተውቃለህ
እልሁን ፡ ተውና ፡ ታረቀኝ ፡ ልጄ ፡ ነህ

አዝ፦ ከሸካራው ፡ መንገድ ፡ እግርህን ፡ መልሰው
አይበጅህምና ፡ ደሜን ፡ አትርገጠው
ይልቅ ፡ እንታረቅ ፡ ምህረቴ ፡ ብዙ ፡ ነው

ምህረት ፡ ተነስታለች ፡ ልቤ ፡ ተናውጣለች
እጄ ፡ ተዘርግታ ፡ ገና ፡ ትኖራለች
የፍቅር ፡ ቀንበሬን ፡ ናና ፡ ልጫንብህ
ጫንቃህንም ፡ ስጠኝ ፡ ዳግም ፡ ልረስብህ

አዝ፦ ከሸካራው ፡ መንገድ ፡ እግርህን ፡ መልሰው
አይበጅህምና ፡ ደሜን ፡ አትርገጠው
ይልቅ ፡ እንታረቅ ፡ ምህረቴ ፡ ብዙ ፡ ነው