ማን ፡ እንዳንተ (Man Endante) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(10)

አዎን ፡ ይሆናል
(Awon Yehonal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ልከፍለው ፡ የማልችል ፡ ነበረብኝ ፡ ዕዳ
ችግሬን ፡ ባዋየው ፡ ማን ፡ እኔን ፡ ሊረዳ
ኃጥያተኛ ፡ ብሎኝ ፡ ሁሉም ፡ ተጸየፈኝ
እንዲፈረድብኝ ፡ ጠላትም ፡ ከሰሰኝ (፪x)

ማነው ፡ የሚያድነኝ ፡ ከእንግዲህ ፡ ብዬ
ብቻዬን ፡ ሳለቅስ ፡ አገኘኝ ፡ ጌታዬ
ዕዳዬን ፡ ተወልኝ ፡ እንባዬን ፡ አበሰው
የሕይወቴን ፡ ቁስል ፡ በቁስሉ ፡ ፈወሰው (፪x)

ብዙ ፡ ኃጥያቴ ፡ ተሰርዮልኛል
አብዝቼ ፡ እንድወደው ፡ በእርግጥ ፡ ይገባኛል
ዋጋው ፡ የከበረ ፡ የሽቶ ፡ መስዋዕት
ከደስታ ፡ እንባ ፡ ጋር ፡ ምነው ፡ ባቀርብለት (፪x)

ለቅሶዬን ፡ ለደስታ ፡ እርሱ ፡ ከለወጠው
ሽቶ ፡ ላፈስለት ፡ ብልቃጡን ፡ ብሰብረው
ማነው ፡ ቅር ፡ የሚሰኝ ፡ ጌታዬን ፡ ባከብረው
ሃብቴን ፡ ብቻ ፡ ሳይሆን ፡ ሕይወቴን ፡ ብሰጠው (፪x)

ማንም ፡ በውድቀቴ ፡ ያላዘነልኝን
በምድር ፡ ላይ ፡ ፍፁም ፡ ተስፋ ፡ የሌለኝ
ሞቴን ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ መለሰው ፡ ኢየሱስ
ስለፍቅርህ ፡ ብዛት ፡ ሥምህን ፡ ልቀድስ (፪x)

ማን ፡ እንዳንተ ፡ ጌታ ፡ ልብን ፡ ሊመረምር
ማን ፡ ጠልቆ ፡ ሊረዳ ፡ የሰዎችን ፡ ችግር
ዕውቀትህ ፡ የላቀ ፡ መሃሪዬ ፡ ነህ
ምሥጋናና ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ለሥምህ
ይሁን ፡ ለሥምህ (፪x)

ይሁን ፡ ለሥምህ (፪x)