ኦ ፡ ክብር (Oh Keber) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Tesfaye Gabisso Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(Meheretu Ayalqemena)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፯ (1987)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 3:26
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ ኦ ፡ ክብር (፬x) ፡ ሃሌሉያ
ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ ለሆነው ፡ አንበሳ ፡ ለሌለው ፡ አምሳያ
ልበል ፡ ላመሥግነው ፡ ከአንጀቴ
ውለታው ፡ ስለበዛ ፡ ይህ:መድኃኒቴ

ሳላውቀው ፡ ያወቀኝ ፡ ሳልሻው ፡ ያዳነኝ
በአስገራሚ ፡ ፍቅሩ ፡ እኔን ፡ የወደደኝ
ከጥፋት ፡ ሩጫ ፡ ነፍሴን ፡ የመለሳት
ኢየሱስ ፡ ነውና ፡ ያወጣኝ ፡ ከእሳት


በልጅነቴ ፡ ጊዜ ፡ ያኔ ፡ በለጋነት
ጠላት ፡ ሲጐትተኝ ፡ ወደዚያ ፡ ባርነት
ፀጋው ፡ ባይበዛልኝ ፡ እጁ ፡ ባይደግፈኝ
የት ፡ ቦታ ፡ ነበርኩኝ ፡ ክንፉ ፡ ባይጋርደኝ


ጥሩር ፡ ሆኖልኛል ፡ በጦርነት ፡ ጊዜ
ፍላጻ ፡ ሲያቆስለኝ ፡ በሃዘን ፡ በትካዜ
ውለታውን ፡ እያሰብኩ ፡ ላመሥግነው ፡ ጌታን
አይገኝምና ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ የሚረዳኝ