From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ (Tesfaye Gabisso)
|
|
ልዩ ፡ እትም (Esp)
|
አልበም (Vol 4)
|
ቁጥር (Track):
|
፱ (9)
|
ርዝመት (Len.):
|
3:43
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች (Albums by Tesfaye Gabisso)
|
|
<poem>
በባቢሎን ፡ ወንዞች ፡ ማዶ ፡ አዝነን ፡ ተቀምጠን
ጽዮንን ፡ ባሰብናት ፡ ጊዜ ፡ እጅግ ፡ አለቀስን
የመጽናናት ፡ አምላክ ፡ ከላይ ፡ ግን ፡ ያየናል
እንባችንን ፡ ጠርጐ ፡ ስብራታችንን ፡ ይጠግንልናል
አዝ፦ ምህረቱ ፡ አያልቅምና
ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነውና
የማዳን ፡ ኃይሉን ፡ ላሳየን
በክንዱ ፡ ለሚጐበኘን
መልካሙን ፡ መዓዛ ፡ በምሥጋና ፡ አቅርቡለት
በዕልልታ ፡ ስገዱለት
የችግረኞችን ፡ ጩኸት ፡ ሰምቶ ፡ አይጨክንም
ምርጦቹን ፡ ከልቡ ፡ በፍፁም ፡ አያስጨንቅም
ጠላታቸው ፡ ሊበትን ፡ በነጐድጓድ ፡ አንቀጥቅጦ
ረድኤታቸው ፡ ከተፍ ፡ ይላል ፡ ከሰማያት ፡ በግርማው ፡ ተገልጦ
አዝ፦ ምህረቱ ፡ አያልቅምና
ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነውና
የማዳን ፡ ኃይሉን ፡ ላሳየን
በክንዱ ፡ ለሚጐበኘን
መልካሙን ፡ መዓዛ ፡ በምሥጋና ፡ አቅርቡለት
በዕልልታ ፡ ስገዱለት
በሥጋዎቻቸው ፡ የገነኑ ፡ ፈፅመው ፡ ሲወድቁ
እግዚአብሔርን ፡ በመታመን ፡ የሚጠባበቁ
በእንባቸው ፡ ፍሬ ፡ እያሸበረቁ
በክንፍ ፡ ይወጣሉ ፡ ይሮጣሉ ፡ ይከብራሉ ፡ እንደ ፡ ዕንቁ
አዝ፦ ምህረቱ ፡ አያልቅምና
ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነውና
የማዳን ፡ ኃይሉን ፡ ላሳየን
በክንዱ ፡ ለሚጐበኘን
መልካሙን ፡ መዓዛ ፡ በምሥጋና ፡ አቅርቡለት
በዕልልታ ፡ ስገዱለት
ለእኛ ፡ መጠጊያችን ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔራችን
በምንም ፡ አንፈራም ፡ እርሱ ፡ ኃይላችን ፡ ነው
ከሰይጣን ፡ አሽክላ ፡ ሥሙ ፡ ይጠብቀናል
ለአሞራም ፡ ሳይሰጠን ፡ በክንፎቹ ፡ አዝሎ ፡ ቤቱ ፡ ያገባናል
አዝ፦ ምህረቱ ፡ አያልቅምና
ለዘለዓለም ፡ ቸር ፡ ነውና
የማዳን ፡ ኃይሉን ፡ ላሳየን
|