From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በጉልበቴ ፡ ያለሁ ፡ ገና ፡ ያልተነካሁኝ
በመንገድ ፡ አጠገብ ፡ በውጭ ፡ የታሰርኩኝ
ነጻነት ፡ የሌለኝ ፡ ውርንጫ ፡ ነበርኩኝ
ሳላውቅህ ፡ አውቀኸኝ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ፈታኸኝ
አዝ፦ ተጠፍሬ ፡ ያየኝ ፡ ያለ ፡ ውዴታዬ
ነጻነት ፡ የሰጠኝ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝታዬ
ማነው ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ባለ ፡ ውለታዬ
ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ተመሥገን ፡ ጌታዬ (፪x)
በዚህ ፡ በጉልበቴ ፡ ለአንተ ፡ ክብር ፡ ሮጬ
እባብና ፡ ጊንጡን ፡ በሥምህ ፡ ረግጬ
መሸለሜን ፡ ሰምቶ ፡ ጠላት ፡ አኮረፈ
አንተን ፡ በላዬ ፡ ሲያይ ፡ ጥላው ፡ ተገፈፈ
አዝ፦ ተጠፍሬ ፡ ያየኝ ፡ ያለ ፡ ውዴታዬ
ነጻነት ፡ የሰጠኝ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝታዬ
ማነው ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ባለ ፡ ውለታዬ
ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ተመሥገን ፡ ጌታዬ (፪x)
ከእሥራት ፡ ፈተኸኝ ፡ በእኔ ፡ ልትቀመጥ
ይህን ፡ ታላቅ ፡ ዕድል ፡ ለምስኪኑ ፡ ልትሰጥ
ለመሆኑ ፡ እኔ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ
ይገባኛል ፡ እንዴ ፡ ለዚህ ፡ ልትመርጠኝ
አዝ፦ ተጠፍሬ ፡ ያየኝ ፡ ያለ ፡ ውዴታዬ
ነጻነት ፡ የሰጠኝ ፡ ወዳጅ ፡ አለኝታዬ
ማነው ፡ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ባለ ፡ ውለታዬ
ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ ፡ ተመሥገን ፡ ጌታዬ (፪x)
ሆሴና ፡ በአርያም ፡ እያሉ ፡ ቢጮሁ
ልብሳቸውንና ፡ ቅጠል ፡ ቢያነጥፉ
የነገር ፡ ጀማሪ ፡ አንተ ፡ በላዬ ፡ ነህ
ክብሩ ፡ የራስህ ፡ ነው ፡ ኑር ፡ ዘለዓለም ፡ ከብረህ
ውርጭላው ፡ ተፈትቶ ፡ የክበር ፡ ዕቃ ፡ ሆኗል
ነጻነትን ፡ ሰጥቶት ፡ ጌታው ፡ ከብሮበታል
የተፈታውን ፡ ሳይሆን ፡ የፈታውን ፡ አክብሩ
ሆሳዕና ፡ በሉ ፡ መንገሡንም ፡ አውሩ (፪x)
|