የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት (Yehatiategnawn Tefat) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(7)

አልበም
(ያይሃል (Yayehal) (Vol. 7))

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 3:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ምሕረትና ፡ ዕውነት ፣ ፍቅር ፡ ቸርነት ፡ ከሞላው ፡ ጌታ
ኃጥዕ ፡ በንስሐ ፡ ይቀበል ፡ ይቅርታ
ማንም ፡ እንዳይጠፋ ፡ መድህን ፡ ሞቶልናል
ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ቤዛ ፡ ሆኖልናል

አዝ፦ የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት
እግዚአብሔር ፡ መቼ ፡ ይወዳል?
የተጣለ ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ
በምክሩ ፡ ያስባል ፣ በምክሩ ፡ ያስባል

ሰው ፡ ግን ፡ በውድቀቱ
ለምን ፡ ተስፋውን ፡ ይቆርጣል ፡ ቶሎ?
ለምን ፡ ይቀናዋል ፡ መውረድ ፡ አሽቆልቁሎ?
"ጌታን ፡ እጠብቃለሁ ፣ ቢገድለኝም" ፡ ብሎ
በዕምነት ፡ የሚቆም ፡ አይቀርም ፡ ጐስቁሎ

አዝ፦ የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት
እግዚአብሔር ፡ መቼ ፡ ይወዳል?
የተጣለ ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ
በምክሩ ፡ ያስባል ፣ በምክሩ ፡ ያስባል

የሚወደውን ፡ ልጅ ፡ እግዚአብሔር ፡ ለጥቅሙ ፡ ይቀጣዋል
መክሮ ፡ ይገስጸዋል ፣ ያስተካክለዋል
በአባትነት ፡ ዓይኑ ፡ ይመለከተዋል
ሲፍገመገም ፡ ቢያየው ፣ ፍጥኖ ፡ ይደግፈዋል

አዝ፦ የኃጢአተኛውን ፡ ጥፋት
እግዚአብሔር ፡ መቼ ፡ ይወዳል?
የተጣለ ፡ ሰው ፡ እንኳን ፡ ፈጽሞ ፡ እንዳይጠፋ
በምክሩ ፡ ያስባል ፣ በምክሩ ፡ ያስባል