ፍቅር ፡ ነው ፡ የጐደለኝ (Feqer New Yegodelegn) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(7)

አልበም
(ያይሃል (Yayehal) (Vol. 7))

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 3:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ የጐደለኝ
በደልን ፡ የምቆጥር ፡ ነኝ
ጌታ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ
መራራ ፡ ሥሬን ፡ ቁረጥልኝ
በአንተው ፡ ፍቅር ፡ የጣፈጠ ፡ ሕይወት ፡ ስጠኝ

ትንቢትና ፡ ዕውቀት ፡ መገለጥ ፡ ቢኖረኝ
ተራራን ፡ የሚያፈርስ ፡ ዕምነት ፡ ሁሉ ፡ ባገኝ
በሰዎች ፡ በመላዕክት ፡ ልሳን ፡ ብናገርም
ፍቅር ፡ ግን ፡ ከሌለኝ ፡ ምንም ፡ አይጠቅመኝም

አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ የጐደለኝ
በደልን ፡ የምቆጥር ፡ ነኝ
ጌታ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ
መራራ ፡ ሥሬን ፡ ቁረጥልኝ
በአንተው ፡ ፍቅር ፡ የጣፈጠ ፡ ሕይወት ፡ ስጠኝ

ፍቅር ፡ ይታገሳል ፣ ቸርነት ፡ ያደርጋል
በዕውነት ፡ ደስ ፡ ይለዋል ፣ ዓመጽን ፡ ይጠላል
አይቀናም ፣ አይመካም ፣ ራሱን ፡ ያዋርዳል
እየተበደለ ፡ ሁሉን ፡ ይቅር ፡ ይላል

አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ የጐደለኝ
በደልን ፡ የምቆጥር ፡ ነኝ
ጌታ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ
መራራ ፡ ሥሬን ፡ ቁረጥልኝ
በአንተው ፡ ፍቅር ፡ የጣፈጠ ፡ ሕይወት ፡ ስጠኝ

በአመቺ ፡ ቦታ ፡ ላይ ፡ ጠላቱን ፡ አግኝቶ
በመልካሙ : መንገድ ፡ በፍቅር ፡ ሸኝቶ
በሰላም ፡ የሚሰድ ፡ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ማነው?
ዳዊት ፡ በዘመኑ ፡ ይህን ፡ አደረገው

አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ የጐደለኝ
በደልን ፡ የምቆጥር ፡ ነኝ
ጌታ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ
መራራ ፡ ሥሬን ፡ ቁረጥልኝ
በአንተው ፡ ፍቅር ፡ የጣፈጠ ፡ ሕይወት ፡ ስጠኝ

ጠላቶችህ ፡ ሳለን ፡ ሞትህ ፡ ካስታረቀን
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ፍቅርህ ፡ ሕይወት ፡ ከሰጠኸን
ሕይወት ፡ እንድናተርፍ ፡ ሰውን ፡ ሁሉ ፡ ወድደን
በዕውነተኛው ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ አጥለቅልቀን

አዝ፦ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ የጐደለኝ
በደልን ፡ የምቆጥር ፡ ነኝ
ጌታ ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ
መራራ ፡ ሥሬን ፡ ቁረጥልኝ
በአንተው ፡ ፍቅር ፡ የጣፈጠ ፡ ሕይወት ፡ ስጠኝ