From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
በምድረ ፡ በዳ ፡ ያለኸው
እንደ ፡ አጋር ፡ ያነባኸው
የሚያይህንስ ፡ ብታየው
ፍጻሜህማ ፡ ተስፋ ፡ አለው
አዝ፦ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
ኑሮ ፡ ቢመሳቀልብህ
የያዝኸው ፡ ቢበተንብህ
ጌታም ፡ የተወህ ፡ ሲመስልህ
ጠላትህ ፡ ሲዘብትብህ
አዝ፦ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
ልብህ ፡ ሲያዝን ፡ ሲተክዝ
ለሕይወትህ ፡ ጽኑ ፡ ምርኩዝ
አይዞህ ፡ ባይ ፡ የሚያበረታ
ከቶ ፡ ማን ፡ አለ ፡ እንደ ፡ ጌታ?
አዝ፦ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
ሸክምን ፡ የሚያራግፍ ፡ ጌታ
የችግረኞች ፡ መከታ
ታማኝ ፡ የበጐች ፡ እረኛ
አማኑኤል ፡ አለን ፡ ለእኛ
አዝ፦ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል ፣ ያይሃል
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሃል ፣ በዕውነት ፡ ያይሃል
የአንተ ፡ ነገር ፡ ይገደዋል
ሊታደግህም ፡ ይመጣል
ያይሃል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሃል
ያይሻል ፣ ኢየሱስ ፡ ያይሻል
ያየናል ፣ ኢየሱስ ፡ ያየናል
|