የሠራዊት ፡ ጌታ (Yeserawit Gieta) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው
(Egziabhier Menfes New)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

የሠራዊት ፡ ጌታ ፡ ኃያሉ ፡ መድህኔ
ሲጠብቀኝ ፡ ሳለ ፡ ፍርድና ፡ ኩነኔ
በኃጢአት ፡ ጣር ፡ ስኖር ፡ ተሳስሬ
ከእስራቴ ፡ ፈታኝ ፡ መራኝ ፡ ወደ ፡ አገሬ (፪x)

አዝ፦ በጭንቄ ፡ ተጨንቆ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ተሰቅሎ
ላረባሁት ፡ ልጁ ፡ እንዲያ ፡ ተጐሳቁሎ
ደሙን ፡ አፈሰሰ ፡ በፍቅሩ ፡ ተገዶ
ሕይወቴን ፡ አዳናት ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋርዶ (፪x)

ፍፁም ፡ የማልረባ ፡ ማስተዋል ፡ የሌለኝ
አዳኜን ፡ የማላውቅ ፡ ፍርድ ፡ የሚጠብቀኝ
የሰይጣን ፡ ምርኮኛ ፡ ሸክም ፡ የተጫነኝ
እንዲህ ፡ ያለሁ ፡ ነበር ፡ ጌታ ፡ ሳያገኘኝ (፪x)

አዝ፦ በጭንቄ ፡ ተጨንቆ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ ተሰቅሎ
ላረባሁት ፡ ልጁ ፡ እንዲያ ፡ ተጐሳቁሎ
ደሙን ፡ አፈሰሰ ፡ በፍቅሩ ፡ ተገዶ
ሕይወቴን ፡ አዳናት ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ተዋርዶ (፪x)

ፍርሃት ፡ መጠራጠር ፡ ክፋትና ፡ እርኩሰት
ይወገድ ፡ ትዕቢት ፡ ቅናት ፡ ምቀኝነት
ተንኮልና ፡ ውሸት ፡ ሀሜት ፡ ክፉ ፡ ምኞት
ተደምስሰው ፡ ይጥፉ ፡ በጽዮኑ ፡ አለት (፪x)

ይውደቁ ፡ ይፈጩ ፡ ይድቀቁ ፡ በአንድነት
ቀንበሩ ፡ ተሰብሯል ፡ ይቅርብኝ ፡ ባርነት
ዕዳዬም ፡ ተከፍሎ ፡ ታውጇል ፡ አርነት
ሞትም ፡ አያስፈራኝ ፡ ተሰጥቶኛል ፡ ሕይወት (፪x)