እንዴት ፡ ዊኪመዝሙርን ፡ ለመጠቀም (How to use WikiMezmur)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search


የዘማሪ ፡ ሥም ፡ ለመጨመር

 1. ወደ ፡ መዘምራን (Gospel Singers) ፡ ድረ ፡ ገፅ ፡ ይሂዱ ።
 2. ከገፁ ፡ ላይ ፡ በቀኝ ፡ በኩል ፡ "ዘማሪ ፡ ይጨምሩ" ፡ የሚለውን ፡ ይጫኑ ።
 3. በሚከፈተው ፡ ማስገቢያ ፡ ውስጥ ፡ የዘማሪውን ፡ ሥም ፡ በአማርኛ ፡ እና ፡ በእንግሊዘኛ ፡ ይጻፉ ።
 4. ሲጨርሱ ፡ በገፁ ፡ ወደታች ፡ የሚገኘውን ፡ "ገጹን ፡ አስቀምጥ" ፡ ወይም ፡ "Save Page" ፡ የሚለውን ፡ ይጫኑ ።

አዲስ ፡ አልበም ፡ ለመጨመር

 1. ወደሚፈልጉት ፡ ዘማሪ ፡ ወይም ፡ መዘምራን ፡ ቡድን ፡ ድረ ፡ ገፅ ፡ ይሂዱ ።
 2. በዘማሪው ፡ ገፅ ፡ በላይ ፡ በቀኝ ፡ በኩል ፡ "አልበም ፡ ይጨምሩ" ፡ የሚለውን ፡ ይጫኑ ።
 3. የሚከፈተው ፡ ገፅ ፡ የተለያዩ ፡ መረጃ ፡ ማስገቢያዎች ፡ አሉት ። ተገቢውን ፡ መረጃ ፡ በአማርኛ ፡ እና ፡ በእንግሊዘኛ ፡ ይጻፉ ። የሚከተሉት ፡ ግዴታ ፡ አስፈላጊ ፡ ናቸው፡-
  1. አልበም (ሥም)
  2. Album (Name)
  3. መዝሙር ፡ ሥሞች
  4. Track (Song) names
 4. የሚከተሉት ፡ ግዴታ ፡ አይደሉም ። ቢኖሩ ፡ ግን ፡ በጣም ፡ ይጠቅማሉ ።
  1. ዓ.ም. (እንደ ፡ ኢትዮጵያውያን ፡ አቆጣጠር)
  2. Year (እንደ ፡ አውሮፓውያን ፡ አቆጣጠር)
  3. Volume (ይሄ ፡ ከሌለ ፣ የአልበም ፡ ሥዕሉ ፡ አይታይም)
  4. ቤተክርስቲያን (የዘማሪው)
  5. Church
  6. (Song) Length
  7. Vendors (የአልበሙ ፡ ሻጮች)
 5. ሥራዎን ፡ ለማየት ፡ በገፁ ፡ ወደታች ፡ የሚገኘውን ፡ "ቅድመ ፡ እይታ" ፡ ወይም ፡ "Show Preview" ፡ ይጫኑ ።
  የመዝሙር ፡ ሥሞቹ ፡ በቀይ ፡ ቀለም ፡ ናቸው ። ይህ ፡ የሚያመለክተው ፡ የመዝሙር ፡ ግጥሞቹ ፡ ገና ፡ እንዳልተጻፉ ፡ ነው ።
 6. ቅድመ ፡ እይታው ፡ ትክክል ፡ ከሆነ ፡ "ገጹን ፡ አስቀምጥ" ፡ ወይም ፡ "Save Page" ፡ የሚለውን ፡ ይጫኑ ።


ማሳሰቢያ፡- ያስተውሉ ፣ የሚከተሉት ፡ ቦታዎች ፡ ከመጡበት ፡ ገፅ ፡ አስቀድመው ፡ ተሞልተዋል ። እነዚህን ፡ መረጃዎች ፡ መቀየር ፡ ከፈለጉ ፡ በመጀመሪያ ፡ የዘማሪው ፡ ገፅ ፡ ላይ ፡ ይቀይሯቸው ።
 1. ዘማሪ
 2. Artist
 3. ሌላ ፡ ሥም (optional)
 4. Nickname (optional)


ማስታወቂያ፡- አልበም ፡ ሲጨምሩ ፣ የራሱ ፡ ገፅ ፡ ነው ፡ የሚሰራለት ። የተጨመረውን ፡ መረጃ ፡ በዊኪመዝሙር ፡ አስተዳዳሪ ፡ እስከሚያረጋገጥ ፡ ድረስ ፡ የዘማሪው ፡ ወይም ፡ የመዘምራን ፡ ቡድኑ ፡ ድረ ፡ ገፅ ፡ ላይ ፡ አይታይም ።


አዲስ ፡ ግጥም ፡ ለመጨመር

 1. ወደሚፈልጉት ፡ ዘማሪ ፡ ወይም ፡ የዘማሪ ፡ አልበም ፡ ድረ ፡ ገፅ ፡ ይሂዱ ።
 2. በገፁ ፡ ላይ ፡ መጨመር ፡ የሚፈልጉትን ፡ የመዝሙር ፡ ሥም ፡ ፈልገው ፡ ያግኙ ።
  1. የመዝሙሩ ፡ ሥም ፡ ሰማያዊ ፡ ቀለም ፡ ከሆነ ፡ የመዝሙር ፡ ግጥሙ፡ ቀድሞ ፡ ተጽፏል ፡ ማለት ፡ ነው ።
  2. የመዝሙሩ ፡ ሥም ፡ ቀይ፡ ቀለም ፡ ከሆነ ፡ የመዝሙር ፡ ግጥሙ ፡ ገና ፡ አልተጻፈም ፡ ማለት ፡ ነው ።
 3. በቀይ ፡ ቀለም ፡ የተጻፈውን ፡ የመዝሙር ፡ ሥም ፡ ይጫኑ ።
 4. የሚከፈተው ፡ ገፅ ፡ የተለያዩ ፡ መረጃ ፡ ማስገቢያዎች ፡ አሉት ። "Lyrics" ፡ የሚለው ፡ ትልቅ ፡ ሳጥን ፡ ውስጥ ፡ ይጫኑ ።
 5. ቋንቋውን ፡ ከእንግሊዘኛ ፡ ወደ ፡ አማርኛ/ትግርኛ ፡ ለመቀየር ፡ ጣት ፡ ሰሌዳው (keyboard) ፡ ላይ ፡ "Ctrl + m" ይጫኑ ።
 6. የመዝሙር ፡ ግጥሙን ፡ ይጻፉ ።
 7. ሥራዎን ፡ ለማየት ፡ በገፁ ፡ ወደታች ፡ የሚገኘውን ፡ "ቅድመ ፡ እይታ" ፡ ወይም ፡ "Show Preview" ፡ ይጫኑ ።
 8. ቅድመ ፡ እይታው ፡ ትክክል ፡ ከሆነ ፡ "ገጹን ፡ አስቀምጥ" ፡ ወይም ፡ "Save Page" ፡ የሚለውን ፡ ይጫኑ ።


ማሳሰቢያ፡- ያስተውሉ ፣ የሚከተሉት ፡ ቦታዎች ፡ ከመጡበት ፡ ገፅ ፡ አስቀድመው ፡ ተሞልተዋል ። እነዚህን ፡ መረጃዎች ፡ መቀየር ፡ ከፈለጉ ፡ ከመጡበት ፡ ገፅ ፡ ላይ ፡ ይቀይሯቸው!
 1. ዘማሪ
 2. Artist
 3. ሌላ ፡ ሥም (optional)
 4. Nickname (optional)
 5. አልበም (ሥም)
 6. Album (name)
 7. ዓ.ም. (እንደ ፡ ኢትዮጵያውያን ፡ አቆጣጠር)
 8. Year (እንደ ፡ አውሮፓውያን ፡ አቆጣጠር)
 9. Volume (ይሄ ፡ ከሌለ ፣ የአልበም ፡ ሥዕሉ ፡ አይታይም)
 10. መዝሙር ፡ ሥም
 11. Title (track/song name)
 12. Track (number)
 13. Length (optional)


ቀድሞ ፡ የተጻፈን ፡ ግጥም ፡ ለማረም

Editing Lyrics
 1. በገፁ ፡ በላይ ፡ ቀኝ ፡ በኩል ፡ "Edit" ፡ የሚለውን ፡ ይጫኑ ።
 2. ማረም ፡ የሚፈልጉትን ፡ ያርሙ ።
 3. ሥራዎን ፡ ለማየት ፡ በገፁ ፡ ወደታች ፡ የሚገኘውን ፡ "ቅድመ ፡ እይታ" ፡ ወይም ፡ "Show Preview" ፡ ይጫኑ ።
 4. ቅድመ ፡ እይታው ፡ ትክክል ፡ ከሆነ ፡ "ገጹን ፡ አስቀምጥ" ፡ ወይም ፡ "Save Page" ፡ የሚለውን ፡ ይጫኑ ።

የአማርኛና ፡ ትግርኛ ፡ መጻፊያ ፡ አቋራጭ ፡ መንገዶች

Command Input Output
አማርኛ/እንግሊዘኛ ፡ ቋንቋ ፡ ለመቀያየር Ctrl + m
ለማስመር u + SPACE
/
<u>
</u>
አዝማች አዝ + SPACE :<u>አዝ</u>፦
ገባ ፡ ለማድረግ :: ::
ድግግሞሽ 2x
3x
...
(፪x)
(፫x)
...

የመዝሙር ፡ ጥቅሶችን ፡ ለመጨመር

<ref>ዘፍጥረት ፩ ፡ ፫ - ፭ (Genesis 1:3-5)</ref>

የዮቱብ ፡ ተንቀሳቃሽ ፡ ፊልም ፡ ለመጨመር

Editing Lyrics
 1. የሚፈልጉትን ፡ ቪዲኦ ፡ ዩትዩብ ፡ ገጽ ፡ አድራሻ ፡ ይያዙ።
 2. በግራ ፡ ያለው ፡ ፎቶ ፡ ምሳሌ ፡ ይሁኖት ። ይህ ፡ የቪዲዮው ፡ ID ፡ ነው ። ፡ ይህን ፡ ኮፒ ፡ ያድርጉ ።
 3. ከዚህም ፡ በኋላ ፡ ID ፡ ቁጥሩን ፡ እዚህ ፡ ኮድ ፡ ጋር ፡ በኮከቦቹ ፡ ምትክ ፡ ይቀይሩ።

{{#widget:YouTube|id=************}}