ክርስቲያን ፡ ተሻገረ (Christian Teshagere) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(3)

ክርስቲያን ፡ ተሻገረ
(Christian Teshagere)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አብን ፡ በዙፋኑ ፡ ወልድን ፡ በስተቀኙ
በምድር ፡ የተገፋውን ፡ በክብር ፡ ሊገናኙ
ፍሬ ፡ አፍርቶ ፡ ታይቶት ፡ ክርስቲያን ፡ በቃሉ
ተፈፀመ ፡ ብሎ ፡ ወጣ ፡ ከሃሩሩ

አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆም
ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ

እውር ፡ ፈሪሳውያን ፡ በምናቸው ፡ ይዩ
ብርሃን ፡ መፈንጠቁን ፡ ከችግር ፡ ይዩ
በመከራ ፡ ናዳ ፡ በሰዎች ፡ ጫጫታ
ሩጫውን ፡ አከተመ ፡ ጀግናው ፡ ሳይረታ

አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆም
ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ

ሃገር ፡ ሃገር ፡ ሲዞር ፡ ሲንከራተት ፡ ከርሞ
መልኩ ፡ ተቀይሮ ፡ በመከራ ፡ ከስሞ
ከጅራፍ ፡ ከዱላ ፡ ከጨካኞች ፡ ጡጫ
ክርስቲያን ፡ አንቀላፋ ፡ አረፈ ፡ ከእርግጫ

አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆም
ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ

እንደነ ፡ ያዕቆብ ፡ በደም ፡ ተበክለን
ለወንጌል ፡ ሊደፉ ፡ ለቃልኪዳናቸው
በሰልፍ ፡ ቆመዋል ፡ ተራ ፡ ይጠብቃሉ
ኢየሱስ (፫x) ፡ ይላሉ

አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆም
ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ