From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ በክቡር ፡ ደሙ ፡ ተዋጅተን
የእጁ ፡ ብጐች ፡ የሆንን
ሥሙን ፡ ከፍ ፡ እያደረግን ፡ ጌታችንን ፡ እናምልከው
በደስታ ፡ እየዘመርን ፡ በዕልልታ ፡ እናንግሰው
በእግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ተንበርክከን
ነውር ፡ የሌለበትን ፡ መስዕዋት ፡ አቅርበን
በእርሱ ፡ ባደረገ ፡ በፈጠረን
በአምላካችን ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይበለን (፪x)
አዝ፦ በክቡር ፡ ደሙ ፡ ተዋጅተን
የእጁ ፡ ብጐች ፡ የሆንን
ሥሙን ፡ ከፍ ፡ እያደረግን ፡ ጌታችንን ፡ እናምልከው
በደስታ ፡ እየዘመርን ፡ በዕልልታ ፡ እናንግሰው
ጌታ ፡ ስናመልከው ፡ ደስ ፡ ይለዋል
ስናመሰግነው ፡ ክብሩ ፡ ይጋርደናል
እህል ፡ ውኃችን ፡ ይባረካል
ለበሽታችንም ፡ ፈውስ ፡ ይሆናል (፪x)
አዝ፦ በክቡር ፡ ደሙ ፡ ተዋጅተን
የእጁ ፡ ብጐች ፡ የሆንን
ሥሙን ፡ ከፍ ፡ እያደረግን ፡ ጌታችንን ፡ እናምልከው
በደስታ ፡ እየዘመርን ፡ በዕልልታ ፡ እናንግሰው
ሩጫን ፡ አብዝተናል ፡ ያለመጠን
ነፍሳችን ፡ ደረቀች ፡ አምልኮ ፡ አስቅርተን
እንድንለመልም ፡ አቆጥቁጠን
ጌታንን ፡ እናምልከው ፡ አስቀድመን (፪x)
አዝ፦ በክቡር ፡ ደሙ ፡ ተዋጅተን
የእጁ ፡ ብጐች ፡ የሆንን
ሥሙን ፡ ከፍ ፡ እያደረግን ፡ ጌታችንን ፡ እናምልከው
በደስታ ፡ እየዘመርን ፡ በዕልልታ ፡ እናንግሰው
|