ከእግርህ ፡ ሥር ፡ መሆን (Kegreh Ser Mehon) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(5)

የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ
(Yenazretu Eyesus)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:05
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

በብዙ ፡ ነገር ፡ እንታወካለን
ኑሮ ፡ ልንገፋ ፡ እንጨነቃለን
በሥጋ ፡ በነፍስ ፡ እንባክናለን
አርፎ ፡ መቀመጥን
ከአንተም ፡ አፍ ፡ መስማትን
ገና ፡ አሁን ፡ ተረዳን ፡ ሰምቶ ፡ መታዘዝን

አዝ፦ ከእግርህ ፡ ሥር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው
ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው
የማይጠፋም ፡ እድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x)

ሲሰሙህ ፡ ደስ ፡ እንደሚልህ ፡ ጌታችን
የአውራ ፡ በግ ፡ ስብ ፡ ብንሰጥህ ፡ ከእጃችን
ምንም ፡ አያረካህ ፡ እንደ ፡ መስማታችን
የእኛ ፡ ብቻ ፡ ይሰማ ፡ እያሉ ፡ መለፍለፍ
መስማትን ፡ ያግዳል ፡ ተናግሮ ፡ አለማረፍ

አዝ፦ ከእግርህ ፡ ሥር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው
ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው
የማይጠፋም ፡ እድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x)

ደቀ ፡ መዝሙርም ፡ ሳይሆን ፡ ከቶ ፡ ሳይማር
እራሱን ፡ የሚሾም ፡ ከሹመቱ ፡ ሲሻር
ብቻውን ፡ ሲወድቅ ፡ ያለ ፡ አንዳች ፡ አጋር
ተግሳፅን ፡ ያገኛል ፡ ጠቢብ ፡ አስተውሎ
ልማር ፡ አስቀድሜ ፡ ሩጫ ፡ ይቆይ ፡ ብሎ

አዝ፦ ከእግርህ ፡ ሥር ፡ መሆን ፡ ግሩም ፡ ነው
ቃልህን ፡ መማር ፡ መልካም ፡ ነው
የማይጠፋም ፡ እድል ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ (፪x)