From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ እታገላለሁ ፣ እታገላለሁ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ እታገላለሁ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ድል ፡ እንደሚሰጠኝ ፡ እምናለሁ
ጉልበቴን ፡ አጠንክሬ ፡ ክንዶቼን ፡ አበርትቼ
እጓዛለሁ ፡ በደስታ ፡ ሳይከፋኝ ፡ ተፅናንቼ
አዝ፦ እታገላለሁ ፣ እታገላለሁ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ እታገላለሁ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ድል ፡ እንደሚሰጠኝ ፡ እምናለሁ
የሰላምን ፡ ወንጌል ፡ በእግሬ ፡ ተጫምቼ
በክንፉ ፡ ተማምኜ ፡ በደሙም ፡ ተሸፍኜ
አዝ፦ እታገላለሁ ፣ እታገላለሁ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ እታገላለሁ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ድል ፡ እንደሚሰጠኝ ፡ እምናለሁ
ፍላጻ ፡ የማይበሳውን ፡ ጥሩሩን ፡ እልብሳለሁ
ሕይወቴን ፡ ላላስድፍር ፡ በተጠንቀቅ ፡ ቆማለሁ
አዝ፦ እታገላለሁ ፣ እታገላለሁ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ እታገላለሁ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ድል ፡ እንደሚሰጠኝ ፡ እምናለሁ
እምነት ፡ ጋሻቸው ፡ ሆኖ ፡ ቅዱሳን ፡ ከተጓዙ
ኑሯቸው ፡ ከተቃና ፡ ድልን ፡ ከተቀዳጁ
አዝ፦ እታገላለሁ ፣ እታገላለሁ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ እታገላለሁ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ድል ፡ እንደሚሰጠኝ ፡ እምናለሁ
በመታገል ፡ ከሆነ ፡ ማሸነፍ ፡ ድል ፡ መንሳት
ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዢ ፡ ጋራ ፡ ከክፋትም ፡ ሠራዊት
አዝ፦ እታገላለሁ ፣ እታገላለሁ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ እታገላለሁ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ድል ፡ እንደሚሰጠኝ ፡ እምናለሁ
የተዘጋጀልኝን ፡ ከኢየሱስ ፡ ከጌታዬ
እወስዳለሁ ፡ አክሊሌን ፡ በሚገባ ፡ ታግዬ
አዝ፦ እታገላለሁ ፣ እታገላለሁ
እስከ ፡ መጨረሻው ፡ እታገላለሁ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ድል ፡ እንደሚሰጠኝ ፡ እምናለሁ
Italic text
|