አየሁ (Ayehu) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው
(Egziabhier Menfes New)

ቁጥር (Track):

፲ ፭ (15)

ርዝመት (Len.): 6:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አየሁ (፫x) ፡ አሻግሬ ፡ አየሁ
አምነው ፡ የሞቱትን ፡ ልመስል ፡ ተመኘሁ

አብርሃምን ፡ አየሁ ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ወዳጅ
ይስሐቅን ፡ ሊሰዋ ፡ ለሰይፍ ፡ የሚያዘጋጅ
ቃሉን ፡ ያከበረ ፡ ያን ፡ ቁም ፡ ነገረኛ
በሀሳቡም ፡ ቁርጠኛ ፡ የእምነትን ፡ አርበኛ
ስውር ፡ ጣዖት ፡ የለውም ፡ ከአምላኩ ፡ የሚነጥል
በቀውጢ ፡ ዘመናት ፡ እምነቱን ፡ የሚያስጥል

ሐዋርያትን ፡ አየሁ ፡ የፅድቅን ፡ ሰልፈኞች
የኃጢአትን ፡ ጠሮች ፡ የእምነትን ፡ ቀንድኞች
በአንድነት ፡ ፀሎት ፡ ምድርን ፡ ነቀነቋት
በድል ፡ ብርሃን ፡ ወንጌል ፡ ባንዴ ፡ አጥለቀለቋት
ከጌቶቹ ፡ ጌታ ፡ ፈቃድ ፡ ነበራቸው
ሥልጣናት ፡ አልቻሉም ፡ ከቶ:ሊያግቷቸው

ሰማዕታትን ፡ አየሁ ፡ እነ ፡ እስጢፋኖስን
ዓለም ፡ ሲጠላቸው ፡ አምነው ፡ ኢየሱስን
የደም ፡ ጥማተኞች ፡ ፍዳ ፡ ሲያሳዯዋቸው
ፊታቸው ፡ ሲያበራ ፡ ያም ፡ ሳይበግራቸው
ለዓለም ፡ ሲያማልዱ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ጌታቸው
አቤት ፡ ሲያስቀና ፡ ያ ፡ አሟሟታቸው

ኮብላዮችን ፡ አየሁ ፡ ከጨለማ ፡ ገብተው
ሲዖልና ፡ ሰይጣን ፡ ጌታም ፡ የለም ፡ ብለው
በሥሙ ፡ ዘብተው ፡ በደሙ ፡ ቀልደው
የለም ፡ ካሉት ፡ ጋራ ፡ በሞት ፡ ተገናኝተው
መንፈሴ ፡ አያቸው ፡ በአንድነት ፡ ሲንጫጩ
በሙታን ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ በእሳት ፡ ሲወራጩ

እንግዲህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔነቴን ፡ ግዛ
ኪዳኔን ፡ አጥፌ ፡ ሞትን ፡ እንዳልገዛ
ብርሃኑ ፡ ደብዝዞ ፡ ጭጋጉ ፡ ሲከበኝ
አንተው ፡ እየመራህ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ አዝልቀኝ
የተፃፈው ፡ ሁሉ ፡ ለትምህርት ፡ ሆኖልኝ
በፅናት ፡ ታግዬ ፡ እንዳሸንፍ ፡ እርዳኝ
የተጻፈው ፡ ሁሉ ፡ ለትምህርት ፡ ሆኖልኝ
ገድሉን ፡ ተጋድዬ ፡ እንዳሸንፍ ፡ እርዳኝ