From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የዓለም ፡ ፍጻሜ ፡ ምልክቶች
የጌታችን ፡ ቃሎች ፡ ትንቢቶቹ
ተፈፅመዋል ፡ የሚበዙቱ
የምጽአቱ ፡ ቀርቧል ፡ ሰዓቱ
አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል
በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል
ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል
ረሃብ ፡ ቸነፈሩ ፡ የምድር ፡ መናወጥ
የአህዛብ ፡ ዕውቀት ፡ መከራና ፡ ምጥ
ፍጥረቱን ፡ ይዞ ፡ ሲያንገዳግደው
የጨለማው ፡ ገዥ ፡ ጨንቆ ፡ ሲያብሰው
አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል
በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል
ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል
ሃሰት ፡ አሰራር ፡ ተዓምራቱ
የዓለም ፡ ሕዝቦችም ፡ ሲሳሳቱ
ዋጋ ፡ ሲያስከፍል ፡ ጌታን ፡ መጥራቱ
ቀኑም ፡ ቅርብ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ንጋቱ
አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል
በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል
ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል
ፍፁም ፡ ባላሰብከው ፡ ሰዓት ፡ ይመጣል
ነቅቶ ፡ መጠበቁ ፡ ይሻልሃል
በምቾት ፡ ወጥመድ ፡ እንዳትታለል
በጸሎት ፡ እየተጋህ ፡ ተጠንቀቅ
አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል
በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል
ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል
ወንጌል ፡ ታውጆ ፡ የዘለዓለም
ሰዎች ፡ አምልጠው ፡ ከጥፋት ፡ ዓለም
የተባረከ ፡ ተስፋችን ፡ ኢየሱስ
ክፉን ፡ ደምስሶ ፡ በድል ፡ ሊነግስ
አዝ፦ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በድንገት ፡ ይመጣል
በሰማይ ፡ ደመና ፡ ከቅዱሳኑ ፡ ጋር ፡ በክብር ፡ ይገለጣል
ፊቱ ፡ ልትቆም ፡ ምን ፡ ያህል (፪x) ፡ ተዘጋጅተሃል
|