From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በሰልፉ ፡ ሜዳ ፡ በዝቶ ፡ ጠላቴ
ፍርሃት ፡ ሲያርደኝ ፡ ፈርቶ ፡ ጉልበቴ
ጠፍሁ ፡ ብዬ ፡ ስል ፡ ወየው ፡ ጌታዬ
ከፊቴ ፡ ያልፋል ፡ ኢየሱስ ፡ ጋሻዬ
አዝ፦ ካፈጠጠብኝ ፡ በዓለም ፡ ካለዉ
እጅግ ፡ ይበልጣል ፡ በእኔ ፡ ያለው
የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ተቆጣጣሪው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ጠላት ፡ እንደ ፡ ንብ ፡ ከቦኝ ፡ ቢመጣ
ምሽጌን ፡ ትቼ ፡ እኔም ፡ አልወጣም
በእግዚአብሔር ፡ ሥም ፡ እሸንፋለሁ
ጐልያድም ፡ ወድቆ ፡ በዓይኔ ፡ አየዋለሁ
አዝ፦ ካፈጠጠብኝ ፡ በዓለም ፡ ካለዉ
እጅግ ፡ ይበልጣል ፡ በእኔ ፡ ያለው
የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ተቆጣጣሪው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ፅኑ ፡ ኃያሉ ፡ የአምላክ ፡ ጦረኛ
አንዱ ፡ ለሺህ ፡ ነው ፡ የእምነት ፡ አርበኛ
ከአመፀኞች ፡ እጅ ፡ ደሙን ፡ በትኖ
ፍሬውን ፡ ያበዛል ፡ በአምላኩ ፡ ታምኖ
አዝ፦ ካፈጠጠብኝ ፡ በዓለም ፡ ካለዉ
እጅግ ፡ ይበልጣል ፡ በእኔ ፡ ያለው
የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ተቆጣጣሪው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው
ረዳት ፡ እንዳለኝ ፡ ጠላቴም ፡ ያያል
እንደ ፡ ዘበተ ፡ መቼ ፡ ይቀራል
የመስቀል ፡ ፅዋ ፡ እኔም ፡ ጠጣለሁ
ድል ፡ ይታወጃል ፡ አሻገራለሁ
አዝ፦ ካፈጠጠብኝ ፡ በዓለም ፡ ካለዉ
እጅግ ፡ ይበልጣል ፡ በእኔ ፡ ያለው
የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ተቆጣጣሪው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)
|