ህዝብህን አብዛህ (Hezbehen Abezah) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(4)

ምሕረቱ አያልቅምና
(Meheretu Ayalqemena)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፹ ፫ (1980)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:29
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ዓላማ ፡ ይዞ ፡ የተሰለፈ ፡ የሚያስፈራ ፡ የአንተ ሰራዊት
ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ እያሸነፈ ፡ በአንተ ፡ መሪነት ፡ ቀንና ፡ ሌሊት
ባሕር ፡ ተሻግሮ ፡ በምድረበዳ ፡ ጊንጡን ፡ ረጋግጦ
ጥቂቱ ፡ ሕዝብህ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ በዝቶ ፡ ርስቱን ፡ ጨበጠ ፡ ከብዙ ፡ በልጦ

ሕዝብን ፡ አበዛህ (፪x)
የአገሪቱንም ፡ ወሰን ፡ አሰፋህ
የማዳን ፡ እጅህን ፡ ለእኛ ፡ ዘረጋህ (፪x)

የሰናፍጯን ፡ ቅንጣት ፡ ቢዘራ ፡ ጌታ ፡ በምድር ፡ እንድትበዛ
ያ ፡ ጉልበተኛ ፡ መጥቶ ፡ ረገጣት ፡ እንዳትበቅል ፡ መስላው ፡ ፈዛዛ
ግን ፡ አልተሳካም ፡ አምልጣ ፡ ወጣች ፡ ሄደች ፡ አደገች
ጌታ ፡ ይመስገን ፡ ድንበሯ ፡ ሰፋ ፡ ለደካከሙት ፡ መጠለያ ፡ ሆነች

ሕዝብን ፡ አበዛህ (፪x)
የአገሪቱንም ፡ ወሰን ፡ አሰፋህ
የማዳን ፡ እጅህን ፡ ለእኛ ፡ ዘረጋህ (፪x)

ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ፡ እያሸነፈ ፡ ዘለዓለም ፡ ነዋሪ
እንደ ፡ አምላካችን ፡ ያለ ፡ ታዳጊ ፡ ከቶ ፡ የት ፡ አለ ፡ ተወዳዳሪ
ጩኸትን ፡ ሰምቶ ፡ ምስኪን ፡ ድሆችን ፡ ዘይት ፡ የሚቀባ
በአደባባዩ ፡ በቤቱ ፡ ተክሎ ፡ የሚያለመልም ፡ እንደ ፡ ዘንባባ

ሕዝብን ፡ አበዛህ (፪x)
የአገሪቱንም ፡ ወሰን ፡ አሰፋህ
የማዳን ፡ እጅህን ፡ ለእኛ ፡ ዘረጋህ (፪x)