From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)
የአመጽ ፡ ፈሳሽ ፡ ሲያስፈራራኝ ፡ የሲዖል ፡ ጣርም ፡ ሲከበኝ
አምላክህ ፡ የታለ ፡ ሲለኝ ፡ ባላንጣዬ ፡ ሲያፌዝብኝ
ከመሠረቴ ፡ ሊነቅለኝ ፡ ቆይ ፡ ብቻ ፡ ሲል ፡ ሲዝትብኝ
የጌታን ፡ ሥም ፡ እጠራለሁ ፡ ከጠላቴም ፡ እድናለሁ
አዝ፦ ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)
የጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለእኔ ፡ የፀና ፡ ግንብ ፡ ነውና
እስከዛሬም ፡ እርሱን ፡ ጠርቶ ፡ ማንም ፡ አላፈረምና
በኪሩቤል ፡ የሚኖረው ፡ ሙሉ ፡ ተስፋ ፡ ስለሰጠኝ
ታምኜ ፡ ሥሙን ፡ እጠራለሁ ፡ ከጠላቴም ፡ እድናለሁ
አዝ፦ ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)
በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ጠራሁት
ስቅስቅ ፡ እያልኩኝ ፡ በእንባ ፡ የሆዴን ፡ ብሶት ፡ ነገርኩት
ከዚያም ፡ በበቀል ፡ ወረደ ፡ ከሰማይ ፡ አንጐደጐደ
በመብረቁ ፡ አወካቸው ፡ በፍላጻው ፡ በተናቸው
አዝ፦ ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)
ለጥርሶቻቸው ፡ ንክሻ ፡ አላደረገኝምና
ከተዘረጋብኝ ፡ ወጥመድ ፡ ሁሌ ፡ አድኖኛልና
አርነቴን ፡ ከሚቀማ ፡ ከሰይጣን ፡ ጋርዶኛልና
ሥሙ ፡ ይክበር ፡ ሃሌሉያ ፡ እያልኩኝ ፡ ልኑር ፡ በእርሱ ፡ ጉያ
አዝ፦ ምሥጋና ፡ የሚገባውን
እግዚአብሔርን ፡ እጠራለሁ
ከጠላቶቼም ፡ እድናለሁ (፪x)
|