በፍፁም ፡ ልባቸው ፡ እንዲያገለግሉት (Befetsum Lebachew Endiyagelegelut) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በፍፁም ፡ ልባቸው ፡ እንዲያገለግሉት
በእርሱና ፡ ለእርሱ ፡ ደግሞ ፡ እንዲኖሩለት
ጌታ ፡ ልጆቹን ፡ ያጠራል ፡ ከኃጢአት ፡ ያነጻቸዋል (፪x)
በእንሰሳት ፡ ፋንድያ ፡ ቤቱ ፡ እንደዚያ ፡ ገምቶ
ያን ፡ የጥንቱን ፡ ጠረን ፡ መዓዛውን ፡ አጥቶ
ኢየሱስ ፡ አያስችለውም ፡ ሳያነጻ ፡ አያልፈውም (፪x)
ከቤተ-መቅደስ ፡ ውስጥ ፡ ሸቀጡን ፡ አራግፎ
የሚቸረችረውን ፡ ነጋዴውን ፡ ገርፎ
አስወጥቶ ፡ ያባርራል ፡ ቅንአቱ ፡ ያቃጥለዋል (፪x)
አብሮ ፡ አደግ ፡ እንክርዳድ ፡ ስንዴውም ፡ ሲታጨድ
አስተዋይ ፡ ገበሬ ፡ ያንን ፡ መንሹን ፡ ሲሰድ
ምርቱን ፡ ከግርዱ ፡ ይለያል ፣ ገለባውን ፡ ለእሳት ፡ ይሰጣል (፪x)
በፍፁም ፡ ልባቸው ፡ እንዲያገለግሉት
በእርሱና ፡ ለእርሱ ፡ ደግሞ ፡ እንዲኖሩለት
ጌታ ፡ ልጆቹን ፡ ያጠራል ፡ ከኃጢአት ፡ ያነጻቸዋል (፪x)
|