ስብራቴ (Seberatie) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(3)

ክርስቲያን ፡ ተሻገረ
(Christian Teshagere)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 5:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

እግሮችም ፡ የሉኝም ፡ ፊትህ ፡ የምቆምበት
ዓይኖችም ፡ የሉኝም ፡ አንተን ፡ የማይበት
የጠራኸኝ ፡ አምላክ ፡ ውርደቴን ፡ ተመልከት
ከገባሁበት ፡ ማጥ ፡ አውጣኝ ፡ በአንተ ፡ ምህረት

አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል
በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል

ከአንተ ፡ የተሰወረ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ፍፁም ፡ ሳይገለጽ ፡ ተደብቆ ፡ የሚቆይ
የልቤ ፡ መርማሪ ፡ የእኔ ፡ ውስጥ ፡ አዋቂ
ጉድለቴን ፡ ይቅር ፡ በል ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂ

አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል
በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል

ምንም ፡ ቸር ፡ ብትሆን ፡ በአንተ ፡ አይዘበትም
ጉዴን ፡ ለመሸፈን ፡ ምክንያት ፡ አላቀርብም
ያው ፡ ከነበደሌ ፡ ራሴን ፡ ሰጥቻለሁ
ምረህ ፡ ተቀበለኝ ፡ ቃልህን ፡ ጥሻለሁ

አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል
በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል

ምንም ፡ እንኳን ፡ ዛሬ ፡ ሃፍረት ፡ ቢሸፍነኝ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ ከቶ ፡ ቢያዳግተኝ
በተስፋ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ቀኔን፡ ጠብቃለሁ
በድል ፡ ልታድሰኝ ፡ እንደምትችል ፡ አምናለሁ

አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል
በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል