ጌታን ፡ ሲጠብቅ (Gietan Sitebeq) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(10)

አዎን ፡ ይሆናል
(Awon Yehonal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:23
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ጌታን ፡ ሲጠብቅ ፡ ታምኖ ፡ የኖረ
ብርሃንን ፡ ሳያይ ፡ ማነው ፡ የቀረ
የነፍስ ፡ ጥማት ፡ ናፍቆትን ፡ ሁሉ
ፀንተህ ፡ ብትቆይ ፡ መልስ ፡ ያገኛሉ

አዝ፦ የጉስቁልና ፡ ዘመን ፡ ያልፍና
ችግር ፡ ስቃይ ፡ ይታሰብና
ጌታ ፡ ዳግመኛ ፡ ይጐበኝሃል
አዲስ ፡ ሰው ፡ አርጐ ፡ ይለውጥሃል (፪x)

ተረስቻለሁ ፡ ተጥያለሁኝ
ለምንም ፡ ነገር ፡ የማልጠቅም ፡ ነኝ
ለምን ፡ ትላለህ ፡ ጌታ ፡ ያስብሀል ፡
በእራሱ ፡ ጊዜ ፡ ከፍ ፡ ያደርግሃል

አዝ፦ የጉስቁልና ፡ ዘመን ፡ ያልፍና
ችግር ፡ ስቃይ ፡ ይታሰብና
ጌታ ፡ ዳግመኛ ፡ ይጐበኝሃል
አዲስ ፡ ሰው ፡ አርጐ ፡ ይለውጥሃል (፪x)

የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ ወዴት ፡ነህ፡ በለው
በፍፁም ፡ ነፍስህ ፡ ተግተህ ፡ ፈልገው
ከቶ ፡ የማይደክም ፡ የማይታክተው
የአባትህ ፡ አምላክ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

አዝ፦ የጉስቁልና ፡ ዘመን ፡ ያልፍና
ችግር ፡ ስቃይ ፡ ይታሰብና
ጌታ ፡ ዳግመኛ ፡ ይጐበኝሃል
አዲስ ፡ ሰው ፡ አርጐ ፡ ይለውጥሃል (፪x)