መቼ ፡ ነው (Mechie New) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(5)

የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ
(Yenazretu Eyesus)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ማለዳ ፡ እየመጣህ ፡ ስታነቃኝ
ጆሮዬን ፡ ከፍተህ ፡ ስትናገረኝ
በማስተዋል ፡ መንገድ ፡ ስትመራኝ
ከሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ ስታረካኝ
ለምልሞ ፡ ነበር ፡ ሕይወቴ
እንዲህ ፡ አልዛለም ፡ ጉልበቴ
እባክህ ፡ አስበኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መድኃኒቴ

አዝ፦ መቼ ፡ ነው ፡ ነቅቼ ፡ ድምጽህን ፡ የምሰማው
ለነፍሴ ፡ መጐብኘት ፡ መጽናናቴ ፡ የሚመጣው (፪x)

በሌሊት ፡ ስነሳ ፡ ከእንቅልፌ
ሥምህ ፡ ነው ፡ የሚመጣው ፡ ፈጥኖ ፡ በአፌ
ህመሜን ፡ ለአንተ ፡ እናገራለሁ
ድምጽህን ፡ አሰማኝ ፡ እማራለሁ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ መቃተቴን ፡ ስማ
ነፍሴ ፡ እንደዚህ ፡ ተዳክማ
እንደ ፡ ምን ፡ ትዘልቃለች ፡ ትካዜን ፡ ተሸክማ

አዝ፦ መቼ ፡ ነው ፡ ነቅቼ ፡ ድምጽህን ፡ የምሰማው
ለነፍሴ ፡ መጐብኘት ፡ መጽናናቴ ፡ የሚመጣው (፪x)

የተወሰነው ፡ ስዓትህ ፡ ሞልቶ
የሀዘኑ ፡ ጊዜ ፡ አብቅቶ
ድካም ፡ ድንዛዜ ፡ ተወግዶ
ኃይልህ ፡ የሚሞላኝ ፡ ከላይ ፡ ወርዶ
መቼ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ የምሰኘው
በጉብኝትህ ፡ የምጽናናው
ጉልበት ፡ ተመልሶ ፡ በእግሬ ፡ የምቆመው

አዝ፦ መቼ ፡ ነው ፡ ነቅቼ ፡ ድምጽህን ፡ የምሰማው
ለነፍሴ ፡ መጐብኘት ፡ መጽናናቴ ፡ የሚመጣው (፪x)