ማደርያዎችህ (Maderiyawocheh) - ተስፍዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፍዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(7)

አልበም
(ያይሃል (Yayehal) (Vol. 7))

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፍዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

ክቡር ፡ ድንጋዮች ፡ ሕያዋን ፡ ልጆች
በበጉ ፡ ደም ፡ የተዋጁ ፡ ሰዎች
ቤተ ፡ መቅደስ ፡ ለመሆን ፡ ታነጹ
ማደሪያ ፡ ሆኑለት ፡ ለንጉሡ

አዝ፦ ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

በዓለም ፡ አዕላፍ ፡ ዕርካታን ፡ ያጡ
ዝናህን ፡ ሰምተው ፡ ከሩቅ ፡ የመጡ
በኃጥአን ፡ ድንኳን ፡ ከሚቀመጡ
በአንተ ፡ ማደሪያ ፡ መጣል ፡ መረጡ
UI
አዝ፦ ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

በጓዳዎችህ ፡ ክቡር ፡ ነገሮች
ተከምረዋል ፡ የሰማይ ፡ ሃብቶች
በመብራት ፡ በዘይትህም ፡ ቅባቶች
እጅግ ፡ ደመቁ ፡ የአንተ ፡ ልጆች

አዝ፦ ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

ካህናቶችህ ፡ በመለከቶች
መዘምራን ፡ በዜማ ፡ ዕቃዎች
ባንድነት ፡ ቃና ፡ ወጣ ፡ ድምጻቸው
ከፍ ፡ አደረጉህ ፡ በምሥጋናቸው

አዝ፦ ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ

በዘለዓለማዊው ፡ ምሕረቱ
ልኡል ፡ ጐበኘን ፡ በቸርነቱ
ጌታ ፡ ለሕዝቡ ፡ ሰጠ ፡ ሞገሱን
የአምላኬ ፡ ክብር ፡ ሞላ ፡ መቅደሱን

አዝ፦ ማደሪያዎችህ ፡ እንደ ፡ ምን ፡ የተወደዱ ፡ ናቸው
በቅዱስ ፡ ቃልህ ፡ በመንፈስህ ፡ የቀደስካቸው
ጌታዬ ፡ ሆይ! በመቅደስህ ፡ ከፍ ፡ ባለውም ፡ ዙፋንህ
ስግደት ፡ ይቅረብልህ ፤ ስግደት ፡ ይቅረብልህ