From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በጌተ ፡ ሰማኒ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቃቶ
በቀራንዮ ፡ ላይ ፡ ከጠላት ፡ ተዋግቶ
በጐቹን ፡ አድኗል ፡ ነፍሱን ፡ ለሞት ፡ ሰጥቶ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ፍቅር ፡ ከየት ፡ ይገኛል ፡ ከቶ (፫x)
መልካም ፡ እረኛ ፡ ስለ ፡ በጐቹ
ነፍሱን ፡ ያኖራል ፡ በእርሱ ፡ የሚገባ
በእርሱም ፡ የሚሰማራ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይድናል
ዘለዓለም ፡ ይኖራል
መንጋውን ፡ ሊበትን ፡ እረኛውን ፡ መቶ
ሰይጣን ፡ ቢጣጣርም ፡ እጅግ ፡ ተበራቶ
ምርኮውንም ፡ መልሷል ፡ ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነስቶ
ዛሬም ፡ ይደግመዋል ፡ ሕዝቦቹን ፡ ጐብኝቶ (፫x)
አዎን ፡ ይሆናል ፡ መቼ ፡ ይቀራል
እንጠብቃለን ፡ ለቅሷችንን ፡ በደስታ
ኢየሱስ ፡ ለውጦልን ፡ ብርሃንን ፡ እናያለን (፪x)
ሃዘንተኞች ፡ ስንሆን ፡ ዘወትር ፡ ደስ ፡ ይለናል
ዓለም ፡ የሌላትን ፡ መድህን ፡ አግኝተናል
ስለዚህም ፡ እኛ ፡ ምንም ፡ ብንገፋ
ማንም ፡ አይጥለንም ፡ ከዚህ ፡ ፅኑ ፡ ተስፋ (፫x)
አዎን ፡ ይሆናል ፡ መቼ ፡ ይቀራል
እንጠብቃለን ፡ ለቅሷችንን ፡ በደስታ
ኢየሱስ ፡ ለውጦልን ፡ ብርሃንን ፡ እናያለን (፪x)
በቅርብ ፡ በሩቅ ፡ የተበተናችሁ
ጌታ ፡ ቅርብ ፡ ነውና ፡ ፍፁም ፡ አይክፋችሁ
የእርሱን ፡ በጐነት ፡ ለዓለም ፡ ተናግራችሁ
ለጽዮን ፡ ስብሰባ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ያብቃችሁ (፫x)
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ና
ናና ፡ ሰብስበን ፡ ከተበታተንበት
ወደ ፡ ውድ ፡ አገራችን ፡ ጥራን ፡ አከማቸን (፪x)
አዎን ፡ ይሆናል ፡ መቼ ፡ ይቀራል
እንጠብቃለም ፡ ለቅሷችንን ፡ በደስታ
ኢየሱስ ፡ ለውጦልን ፡ ብርሃንን ፡ እናያለን (፪x)
አዎን ፡ ይሆናል ፡ (አዎን ፡ ይሆናል)
መቼ ፡ ይቀራል ፡ (መቼ ፡ ይቀራል)
እንጠብቃለን ፡ ለቅሷችንን ፡ በደስታ
ኢየሱስ ፡ ለውጦልን ፡ ብርሃንን ፡ እናያለን (፪x)
|