ከአቅምህ ፡ በላይ (Kaqemeh Belay) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Tesfaye Gabisso Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ምህረቱ ፡ አያልቅምና
(Meheretu Ayalqemena)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 3:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመፍታት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ

በሁለት ፡ ዓሣ ፡ በአምስት ፡ እንጀራ
አምስት ፡ ሺህ ፡ አጠገብክ ፡ በበረሃው ፡ ስፍራ
ዛሬም ፡ አይሳንህም ፡ ይህንን ፡ ልታደርግ
የደካከምነውን ፡ በቃልህ ፡ ልትባርክ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመስራት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ

ለዕብራውያን ፡ መናህን ፡ ያወረድክ
እውር ፡ ያበራህ ፡ ሸባን ፡ በእግሩ ፡ ያቆምክ
ዛሬም ፡ አይሳንህም ፡ ይህንን ፡ ልታደርግ
የዛለውን ፡ ጉልበት ፡ አድሰህ ፡ ልትለቅ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመስራት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ

የትኛው ፡ ደዌ ፡ ለፈውስ ፡ አስቸገረህ
የትኛው ፡ ኃያል ፡ ተቋቁሞ ፡ ያዘህ
የኃያላን ፡ ኃያል ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ
ጠላትህን ፡ ረትተህ ፡ መንፈስህን ፡ አፍስስ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመስራት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ

የሁሉም ፡ ዓይኖች ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ናቸው
ምስኪኖችህን ፡ መጥተህ ፡ ታደጋቸው
ነፍሳትን ፡ ሁሉ ፡ ማዕበሉንም ፡ አዛዥ
በመከራ ፡ ጊዜ ፡ የጻድቃን ፡ አጋዥ

አዝ፦ ከአቅምህ ፡ በላይ ፡ ሆኖ ፡ የሚከብድህ
ለመስራት ፡ ከቶ ፡ የሚያስቸግርህ
ምን ፡ ችግር ፡ አለ ፡ የሚያዳግትህ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ የሆንክ ፡ ኤልሻዳይ ፡ አንተ ፡ ነህ