ሕይወት ፡ ለተጠሙ (Hiwot Letetemu) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው
(Egziabhier Menfes New)

ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:01
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ወንድሞች ፡ በሕብረት ፡ ቢቀመጡ ፡ ቀርበው
ለማነጽ ፡ የሚጠቅም ፡ የፀጋ ፡ ቃል ፡ ይዘው
አፋቸውን ፡ ሲከፍቱ ፡ በክርስቲያን ፡ ቋንቋ
ምንኛ ፡ ደስ ፡ ይላል ፡ ሲቀር ፡ አሉባልታ

አዝ፦ ሕይወት ፡ ለተጠማ ፡ የምሥራች ፡ በሉ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ወደው ፡ ቢቀበሉ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ይሰበካል
የሚያረካ ፡ ምንጭ ፡ ለሁሉም ፡ ተሰብኳል

የመንፈስን ፡ ፍሬ ፡ አዝሎ ፡ በሕይወቱ
የአምላክን ፡ ደራሲ ፡ አውቆ ፡ ማንነቱን
ጌታን ፡ ሲያንፀባርቅ ፡ እስከ ፡ ዕለተ ፡ ሞቱ
ከክበር ፡ ወደ ፡ ክብር ፡ ይለወጣል ፡ ቤቱ

አዝ፦ ሕይወት ፡ ለተጠማ ፡ የምሥራች ፡ በሉ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ወደው ፡ ቢቀበሉ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ይሰበካል
የሚያረካ ፡ ምንጭ ፡ ለሁሉም ፡ ተሰብኳል

ሸክምን ፡ ለማራገፍ ፡ በመስቀሉ ፡ እግር
ክርስቲያን ፡ ሲንበረከክ ፡ ልቡ ፡ ሲሰባበር
ሚስጥሩን ፡ ለጌታ ፡ በእንባ ፡ አወያይቶ
ተፅናንቶ ፡ ይነሳል ፡ በእምነት ፡ ተሞልቶ

አዝ፦ ሕይወት ፡ ለተጠማ ፡ የምሥራች ፡ በሉ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ወደው ፡ ቢቀበሉ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ይሰበካል
የሚያረካ ፡ ምንጭ ፡ ለሁሉም ፡ ተሰብኳል

ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ሕብረቱ ፡ ጠንክሮ
ሕይወት ፡ ሲስተካከል ፡ ግንኙነት ፡ ሰምሮ
ኑሮ ፡ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ዓለምን ፡ ያስንቃል
ለዛ ፡ አለው ፡ ይጥማል ፡ ቢመረጥ ፡ ይበጃል

አዝ፦ ሕይወት ፡ ለተጠማ ፡ የምሥራች ፡ በሉ
እንዲህ ፡ ያለ ፡ ኑሮ ፡ ወደው ፡ ቢቀበሉ
ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ይሰበካል
የሚያረካ ፡ ምንጭ ፡ ለሁሉም ፡ ተሰብኳል