From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ጌቴ ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ቤዛ
ጉስቁልናዬ ፡ ቢበዛ
ከክብሩ ፡ ተዋረደልኝ
በእኔ ፡ ፈንታ ፡ ታረደልኝ (፪x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት
ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት
ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት
በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት
ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት
ግብዝ ፡ አይደል ፡ እንደ ፡ ሰው
ወረት ፡ ጨርሶ ፡ ያልነካው
በጐልጐታ ፡ ላይ ፡ የታየው
እውነትም ፡ እርሱ ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት
ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት
ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት
በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት
ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት
ያጀቡት ፡ ሁሉ ፡ ፈርጥጠው
ለሰይፍ ፡ ለጐመድ ፡ አጋልጠው
በዚያን ፡ ምሽት ፡ አልቦታል
ቃቶ ፡ ነፍሴን ፡ ታድጓታል (፪x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት
ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት
ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት
በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት
ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት
በግፍ ፡ ጀርባው ፡ ተላልጦ
እግሩንም ፡ ለስቃይ ፡ ገልጦ
ንጹስህ ፡ ደሙን ፡ ለእኔ ፡ ከፍሎ
በቀራንዮ ፡ ደርቆ ፡ ውሎ (፪x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት
ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት
ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት
በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት
ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት
ይህ ፡ ፍቅር ፡ በሕይወቴ ፡ ገብቶ
የደህንነት ፡ ሥራ ፡ ሰርቶ
ቆሻሻነቴን ፡ ቀይሮ
አይቻለሁኝ ፡ ውብ ፡ ኑሮ (፪x)
አዝ፦ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ገዶት
ኃጢአቴም ፡ አስጨንቆት
ዝም ፡ ብሎ ፡ እንደ ፡ ጠቦት
በሀሰት ፡ ተመስክሮበት ፡ በችሎት
ዕዳዬን ፡ ከፍሎታል ፡ ተሰቅሎ ፡ በመሞት
|