From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ
እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ
በእምነት ፡ እሻገራለሁ
በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ
ከቀደሙት ፡ ተምሬያለሁ
የአንተን ፡ ተስፋ ፡ ጠብቃለሁ
በእምነትህ ፡ ተመልከተኝ
እምነትንም ፡ ጨምርልኝ
አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ
እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ
በእምነት ፡ እሻገራለሁ
በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ
የፍየልን ፡ ሌጦ ፡ ለብሰው
መቅደስህን ፡ ተንተርሰው
እየተንከራተቱ ፡ ብዙ ፡ አሉ
ክብራቸውን ፡ ለአንተ ፡ የጣሉ
አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ
እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ
በእምነት ፡ እሻገራለሁ
በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ
በእምነት ፡ ሥምህን ፡ ጠሩ
በፀሎት ፡ ለአንተ ፡ ነገሩ
በላይ ፡ ሆነህ ፡ ሰማሃቸው
ቃላቸውን ፡ አደመጥካቸው
አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ
እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ
በእምነት ፡ እሻገራለሁ
በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ
በእምነት ፡ ባሕርን ፡ ከፈቱ
ከጠላት ፡ እጅ ፡ አመለጡ
እነርሱን ፡ ልመስል ፡ እሻለሁ
በእምነት ፡ ሥምህን ፡ ጠራለሁ
አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ
እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ
በእምነት ፡ እሻገራለሁ
በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ
በመንፈስ ፡ መልክትን ፡ ሰሙ
ጌታ ፡ አንተን ፡ ተሳለሙ
እምነትን ፡ ስጠኝ ፡ እራስህ
እኔም ፡ አንተን ፡ ለምናለሁ
አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ
እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ
በእምነት ፡ እሻገራለሁ
በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ
|