ተመለስ (Temeles) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(1)

እግዚአብሔር ፡ ኃያል
(Egziabhier Hayal)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 3:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ተስፋህ ፡ ጨልሞ ፡ ጭንቀት ፡ አስጥሞህ
መጥፋትህ ፡ ታይቶኝ ፡ ከዚያ ፡ ጣር ፡ አወጥቼህ
ደስ ፡ ብሎህ ፡ ነበር ፡ አግኝተህ ፡ እፎይታ
ለምን ፡ ነው ፡ ዛሬስ ፡ የሆንከው ፡ ከርታታ

አዝተመለስ (፫x) ፡ ልጄ ፡ ሆይ (፪x)

በእኔ ፡ ተማምነህ ፡ ስትመላለስ
በእንባ ፡ በፀሎት ፡ ቀርበህ ፡ ስትታደስ
የነበረህ ፡ ወዝ ፡ መልክህስ ፡ የታለ
ናና ፡ ታረቀኝ ፡ ፀጋዬ ፡ እያለ

አዝተመለስ (፫x) ፡ ልጄ ፡ ሆይ (፪x)

የፍቅር ፡ ወንጌል ፡ ለሌላው ፡ ሰብከህ
ሸክማቸው ፡ ከብዶህ ፡ ፡ ለጠፉት ፡ አልቅሰህ
መስክረህ ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ አምጥተህ
ሳይህ ፡ አዝናለሁ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ኮብልለህ

አዝተመለስ (፫x) ፡ ልጄ ፡ ሆይ (፪x)

ቤቴ ፡ ናፍቆህ ፡ ብትመለስልኝ
ይቅርታ ፡ ፈልገህ ፡ ብትመጣልኝ
የምህረት ፡ እጄስ ፡ ተዘርግታለች
የፍቅር ፡ እንባም ፡ ዓይኔ ፡ ታፈሳለች

አዝተመለስ (፫x) ፡ ልጄ ፡ ሆይ (፪x)