ተመሥገን ፡ ጌታዬ (Temesgen Gietayie) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው
(Egziabhier Menfes New)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 3:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን
ተመሥገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x)

በጉለት ፡ እንዲቆይ ፡ ሳይደክም ፡ ጉልበቴ
ኃይልን ፡ አስታጠቀኝ ፡ ከላይ ፡ መድኃኒቴ
በብዙ ፡ ውሽንፍር ፡ ቢያጥለቀልቅ ፡ ጐርፉ
ጠላቶች ፡ በአንተ ፡ ሥም ፡ ሁሉም ፡ ተሸነፉ

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን
ተመሥገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x)

የኑሮዬ ፡ ተገን ፡ ክብሬ ፡ መከታዬ
ኃይሌም ፡ ይታደሳል ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ተድላዬ
ማዕበሉ ፡ ተነስቶ ፡ ሊያሰጥመኝ ፡ ሲቃጣ
በገሀድ ፡ አያለሁ ፡ ረዳቴ ፡ ስትመጣ

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን
ተመሥገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x)

የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ፡ አያልቅም ፡ ቢቆጠር
ነነዌም ፡ ብትሰራ ፡ ኃጢአት ፡ በማግበስበስ
አምላክም ፡ አስቦ ፡ እነርሱን ፡ ለመምከር
አዘዘው ፡ ዮናስን ፡ ለሕዝቡ ፡ እንዲናገር

አዝ፦ ተመሥገን ፡ ጌታዬ
ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን
ተመሥገን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ክብር ፡ ገናንነት ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x)