From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ከዚህም ፡ የሚበልጥ
የጌታ ፡ ኃይል ፡ ሲገለጥ
እናያለን ፡ ገና ፣ የክብሩን ፡ ደመና
ምድር ፡ ስትሞላ ፣ በጌታ ፡ ምሥጋና
ጌታ ፡ በመንፈሱ ፡ በቅሉ ፡ መርምሮ
ሥራችንን ፡ ሁሉ ፡ ቢነግረን ፡ ዘርዝሮ
በዕውቀቱ ፡ ተደንቀን ፣ በኑሮአችን ፡ አፍረን
ንስሐ ፡ ገብተናል ፡ "ይቅር ፡ በለን" ፡ ብለን
አዝ፦ ከዚህም ፡ የሚበልጥ
የጌታ ፡ ኃይል ፡ ሲገለጥ
እናያለን ፡ ገና ፣ የክብሩን ፡ ደመና
ምድር ፡ ስትሞላ ፣ በጌታ ፡ ምሥጋና
ኃጢአታችንን ፡ በደሙ ፡ አነጻው
የእኛ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ነው
ርኩስ ፡ መናፍስትን ፡ በኃይሉ ፡ ያስወጣል
በወንጌሉ ፡ ሥልጣን ፡ መንግሥቱን ፡ ያሰፋል
አዝ፦ ከዚህም ፡ የሚበልጥ
የጌታ ፡ ኃይል ፡ ሲገለጥ
እናያለን ፡ ገና ፣ የክብሩን ፡ ደመና
ምድር ፡ ስትሞላ ፣ በጌታ ፡ ምሥጋና
"ጌታ ፡ ሆይ!" ፡ እያለ ፡ ለሚቃትተው
ማዳኑ ፡ ሊመጣ ፡ ጽድቁ ፡ ሊገለጥ ፡ ነው
የእግዚአብሔር ፡ ምሕረት ፡ ሁሉንም ፡ አብስሩ
የበረከት ፡ ዝናብ ፡ ይኸው ፡ ውሽንፍሩ
አዝ፦ ከዚህም ፡ የሚበልጥ
የጌታ ፡ ኃይል ፡ ሲገለጥ
እናያለን ፡ ገና ፣ የክብሩን ፡ ደመና
ምድር ፡ ስትሞላ ፣ በጌታ ፡ ምሥጋና
ረሃብተኛ ፡ ሲመገብ ፣ ልኡል ፡ ቃሉን ፡ ሲሰጥ
በጻድቅን ፡ ዕልልታ ፡ ምድር ፡ ስትናወጥ
በምሥጋና ፡ ዜማ ፡ በደስታ ፡ ዝማሬ
በታላቁ ፡ መከር ፡ የአገልግሎት ፡ ፍሬ
ከዚህም ፡ የሚበልጥ
የጌታ ፡ ኃይል ፡ ሲገለጥ
እናያለን ፡ ገና ፣ የክብሩን ፡ ደመና
ምድር ፡ ስትሞላ ፣ በጌታ ፡ ምሥጋና
|