መጥቷል ፡ በንስሃ (Metual Beneseha) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Tesfaye Gabisso Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

ምህረቱ ፡ አያልቅምና
(Meheretu Ayalqemena)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:21
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ሊጠፋ ፡ የነበር ፡ በኃጢያቱ ፡ ረክሶ
ለጥቂት ፡ አምልጦ ፡ ከዓለም ፡ ተመልሶ
ማንነቱን ፡ አውቆ ፡ ልብ ፡ ገዝቶ ፡ ኖሮ
ባለፈው ፡ ጥፋቱ ፡ በጸጸት ፡ ተማሮ
መጥቷል ፡ በንስሃም ፡ የጌታን ፡ ቃል ፡ ሰምቶ
ሰይጣንን ፡ ዓለምን ፡ ሥጋን ፡ ተሰናብቶ (፪x)

እንዲያው ፡ ሲግደረደር ፡ ጥማቱን ፡ ደብቆ
የጭንቀቱን ፡ ግፊት ፡ በሆዱ ፡ አምቆ
ሰላምን ፡ ለማግኘት ፡ ሲባዝን ፡ ሰንብቶ
ከሰላም ፡ አለቃም ፡ መንገድ ፡ ተገናኝቶ
አሁን ፡ ወጥቶለታል ፡ ችግሩን ፡ ተንፍሶ
ተጽናንቶም ፡ ይኖራል ፡ ሕይወቱ ፡ ታድሶ (፪x)

ወዶታል ፡ ከአንጀቱም ፡ ተመክቶበታል
ጌታም ፡ በጠላት ፡ ፊት ፡ በዘይት ፡ ቀብቶታል
ከትቢያ ፡ አንስቶ ፡ ሞገስን ፡ ሰጥቶታል
በድል ፡ አየመራው ፡ ከዚህ ፡ አድርሶታል
እንደ ሰባ ፡ እንቦሳም ፡ በደስታ ፡ ይዘላል
እየፈነደቀም ፡ ሀሌሉያ ፡ ይላል (፪x)

ጠቢባን ፡ ግንበኞች ፡ ወደ ፡ ጐን ፡ የጣሉት
አይጠቅመንም ፡ ብለው ፡ በንቀት ፡ የካዱት
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ የማዕዘን ፡ አለት
ሆኖለታል ፡ ለእርሱ ፡ የሕይወት ፡ መሰረት
ከዳንኩኝስ ፡ ብሏል ፡ አዲስ ፡ ሰው ፡ ከሆንኩኝ
ዘመድ ፡ ወዳጆቼ ፡ ያሉትን ፡ ይበሉኝ (፪x)