በደልን ፡ ይቅር ፡ የሚል (Bedelen Yeqer Yemil) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(6)

አቤቱ ፡ መባረክን ፡ ባርከን
(Abietu Mebareken Barken)

ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 2:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

በደልን ፡ ይቅር ፡ የሚል ፡ አመጻን ፡ የሚያሳልፍ
ከጥፋት ፡ ሊያድናቸው ፡ በሕዝቡ ፡ ላይ ፡የሚሰፍፍ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ አምላክ ፡ ማነው ፡ ምህረቱ ፡ የበዛ?
ቅዱሳንህ ፡ ሲሰደዱ ፡ መከራውም ፡ ሲበዛ

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ

የእግዚአብሔር ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፡ተፅፏል ፡ ህዝቡ ፡ ነው  !
ሊያመልከው ፡ ሊያገለግለው ፡ ከግብጽ ፡ አገር ፡ ያፈለሰው
አርነቱን ፡ በባርነት ፡ ሊተካ ፡ የሚከጅለው
"ይገባኛል " ፡ የሚል ፡ ማነው ? ሕዝቡ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው!

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ

እስከዛሬ ፡ከብረሃል ፡ በአህዛብ ፡ ተፈርተሃል
የጠላትን ፡ እርግማን ፡ በረከት ፡ አድርገሃል
የአሳዳጁን ፡ ፈረሶች ፡ በባሕር ፡ አስጥመሃል
በክንድህ ፡ ተከላክለህ ፡ ርስትህን ፡ ጠብቀሃል

አዝ፦ ርስትህን ፡ ለማላገጫ ፡ አሳልፈህ ፡ አትስጥ
የተቀደሰ ፡ መቅደስህን ፡ በጠላት ፡ አታስረግጥ (፪x)