From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በቀራንዮ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ በደዌ ፡ የደቀቀው
ነፍሱን ፡ ስለ ፡ ኃጥያቴ ፡ መስዋዕት ፡ ያደረገው
የሞትን ፡ ቀንበር ፡ ሰብሮ ፡ እኔኑ ፡ ሊያወጣ ፡ ነው
ማዳኑን ፡ ቀምሻለው ፡ ምን ፡ አለ ፡ የምመልሰው (፪x)
አዝ፦ ክብር ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን
አየን ፡ አሸናፊነቱን
ኃያል ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ የለም
ይንገሥ ፡ ለዘለዓለም (፪x)
የተናቀ ፡ ደካማ ፡ ቢመስልም ፡ አመጣጡ
ከእሰይ ፡ ልጅ ፡ ከዳዊት ፡ ሥር ፡ የወጣው ፡ ቁጥቋጡ
ኢየሱስ ፡ አሸነፈ ፡ ፍሬው ፡ ምድርን ፡ ሸፈነ
የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ በእጁ ፡ ተከናወነ (፪x)
አዝ፦ ክብር ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን
አየን ፡ አሸናፊነቱን
ኃያል ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ የለም
ይንገሥ ፡ ለዘለዓለም (፪x)
በደሙ ፡ ኃይል ፡ ጸደቅን ፡ በሥሙ ፡ ድል ፡ አገኘን
ማነው ፡ የሚቋቋመን ፡ ማንስ ፡ ነው ፡ የሚገታን
እንገሰግሳለን ፡ አሸናፊውን ፡ ይዘን
ወደ ፡ ቅድስቷ ፡ ሃገር ፡ በድል ፡ እንገባለን (፪x)
አዝ፦ ክብር ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን
አየን ፡ አሸናፊነቱን
ኃያል ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ የለም
ይንገሥ ፡ ለዘለዓለም (፪x)
ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይዘን ፡ ከፊቱ ፡ እንቀርባለን
በዙፋኑ ፡ ላይ ፡ ላለ ፡ እንሰግድለታለን
ሁሉን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ንገሥ ፡ እንለዋለን
አቤት ፡ ለዘለዓለም ፡ እርሱ ፡ ኃያል ፡ ነው ፡ አሜን (፪x)
አዝ፦ ክብር ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን
አየን ፡ አሸናፊነቱን
ኃያል ፡ እንደ ፡ እርሱ ፡ የለም
ይንገሥ ፡ ለዘለዓለም (፭x)
|