በእምነት ፡ እኖራለሁ (Bemnet Enorelehu) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Tesfaye Gabisso Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(dsfsdf)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (1980)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 3:10
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ከምድር ፡ በላይ ፡ ቢሆን ፡ ከሰማይም ፡ በታች
መግባት ፡ መውጣታችን ፡ ዘወትር ፡ ተመልካች
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ ማንን ፡ አገኛችሁ
የሕይወት ፡ ዋስትና ፡ ጌታ ፡ ሚሆናችሁ

አዝ፦ በእምነት ፡ እኖራለሁ ፡ ጌታዬን ፡ አውቃለሁ
የእኔን ፅኑ አምባ ፡ ተተግኜዋለው
ወጀቡን ፡ ሳልፈራ ፡ ታግዬ ፡ እረታለሁ
የክብር ፡ ሽልማቴን ፡ ከእጁ ፡ እረከባለሁ

ለነገ ፡ አይጨንቀኝም ፡ ጭጋግ ፡ ቢሸፍነው
ወይኑ ፡ ቢጠወልግ ፡ ሃሩሩ ፡ ቢያሰጋው
ለእግሬ ፡ መብራት ፡ ነው ፡ ቃሉ ፡ በእጄ ፡ ያለው
የተፈጥሮ ፡ አዛዥ ፡ ኢየሱስ ፡ ሕያው ፡ ነው

አዝ፦ በእምነት ፡ እኖራለሁ ፡ ጌታዬን ፡ አውቃለሁ
የእኔን ፡ ፅኑ ፡ አምባ ፡ ተተግኜዋለው
ወጀቡን ፡ ሳልፈራ ፡ ታግዬ ፡ እረታለሁ
የክብር ፡ ሽልማቴን ፡ ከእጁ ፡ እረከባለሁ

ፈቃዱ ፡ ሲሞላ ፡ ጌታዬ ፡ ከብሮ ፡ ሳይ
ምድር ፡ ዕልል ፡ ስትል ፡ ስያጨበጭብ: ፡ ሰማይ
መጠለያ ፡ ልብሴ ፡ እንጀራየ ፡ ያ ፡ ነው
ነፍሴ ፡ ትጠግባለች ፡ በክብር ፡ በግርማው

አዝ፦ በእምነት ፡ እኖራለሁ ፡ ጌታዬን ፡ አውቃለሁ
የእኔን ፅኑ አምባ ፡ ተተግኜዋለው
ወጀቡን ፡ ሳልፈራ ፡ ታግዬ ፡ እረታለሁ
የክብር ፡ ሽልማቴን ፡ ከእጁ ፡ እረከባለሁ